የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት አጠቃላይ የሰውነታችን አሰራር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ

የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት አጠቃላይ የሰውነታችን አሰራር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ

(Last Updated On: November 8, 2019)

Hyperthyroidism Affects the Entire Body

 

ታይሮድ በፊት ለፊት አንገታችን ላይ የሚገኝ እጢ ሲሆን ሰውነታችን በሁሉም መልኩ የተስተካከለ አሰራር እንዲኖረው የሚያደርጉ ሆርሞኖችን ያመርታል ይህ እንዲሆን ደግሞአዮዲንየተባለ ንጥረ ነገር ያስፈልገዋል፡፡የአዮዲን መጠን ስተኛ ወይም ከመጠን ማለፍ ደግሞ አጠቃላይ የሰውነታችንን ስርዓት ያውካል፡፡

የታይሮድ እጢ ጥቅሞ

 • ለሰውነታችን እድገት እና መጎልበት
 • ለአእምሮአችን ጤና ስሜታችንን ለማስተካከል
 • የሰውነት ሙቀት እንዲሁም አጠቃላይ አሰራር ለማስተካከል
 • በጣም አስፈላጊ የሆኑ የሰውነታችን ክፍሎች እንደ፡- ልብ፤ጡንቻ፤እና አጥንትን የመሳሰሉ አካላት በትክክል እንዲሰሩ ለማድረግ

የታይሮድ እጢ በፍጥነት የሚሰራ ከሆነ ብዙ ሆርሞን በማምረት የሰውነታችንን ጤነኛ አሰራር እንዲታወክ ሊያደርግ ይችላል

ይህም ችግርሀይፐርታይሮይዲዝምበመባል ይታወቃል፡፡ይህ ችግር ሲያጋጥም በእያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል ላይ የሚያሳየው ምልክት ከሰው ሰው ይለያያል፡፡

ሀይፐር ታይሮይዲዝም የሚያስከትላቸው ችግሮ

 • ልብ፡- ድካም፤የተዛባ የልብ ምት እንዲሁም የልብ ህመም
 • ስርዓተ ነርቭ ፡- የእጅ መንቀጥቀጥ፤ፍርሃት፤የእንቅልፍ ችግር፤እረፍት የማጣት ስሜት እና ትኩረት ማጣት
 • ቆዳ፡- የቆዳ ማላብ፤የጸጉር መነቃቀል፤የታችኛው እግር ማበጥ፤የጥፍር መነቃቀል
 • አይን፡- የአይን ኳስ ከተለመደው በላይ ወደ ፊት መውጣት እምባ መብዛት እንዲሁም መቆርቆር
 • ሜታቦሊክ ሲስተም፡- የክብደት መቀነስ
 • መራቢያ አካ ላይ፡- የወር አበባ መዛባት ወይም የወር አበባ መቅረት
 • ጡንቻ ላይ ፡- የጡንቻ መድከም እንዲሁም የእጅ መንቀጥቀጥ
 • አንገት ፡- የታይሮድ እጢ በመጠን መተለቅ በዚህም ምክኒያት ደግሞ የአንገት ማበጥ

ታይሮቶክሲኮሲስ ምክኒያቶች

 • ሀይፐርታይሮይዲዝም፡- የታይሮድ እጢ የታይሮድ ሆርሞን ከመጠን በላይ ማምረት
 • ታይሮዳይትስ፡- የታይሮይድ እጢ ብግነት እና በዚህም ምክኒያት ከመጠን ያለፈ ሆርሞን ማምረት
 • የታይሮድ ሆርሞን እንዲጨምር አስተዋጽዎ ያላቸውን መድሃኒቶች መውሰድ
 • በእርግዝና ምክኒያት በሚመጣ የጠና ህመም ምክኒያት ከመጠን ያለፈ የታይሮድ ሆርሞን መመረት
 • አንዳንድ ፒቱታሪ እጢ ላይ የሚከሰቱ እባጮች

ታይሮቶክሲኮሲስ እንዴት ይታከማል

 • መድሃኒቶ
 • ራዲዮአክቲቭ አዮዲን ህክምና
 • ቀዶ ጥገና

ሀኪሙ የታካሚውን እድሜ የሰውነት ሁኔታ እንዲሁም የበሽታውን ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት አስፈላጊውን የህክምና አይነት የሚመርጥ ሲሆን ታካሚውም የታዘዘለትን መድሃኒት በአግባቡ በመውሰድ የአዮዲን መጠኑ ከፍ ያለ ምግብን በመቀነስ እና ሲጋራ ባለማጨስ ህክምናው ማገዝ ይኖርበታል

ዶ/ር አሩን ኮንግቾ (በቬጂታኒ ሆስፒታል ኢንዶክሪኒሎጂስት)

Doctor
Dr. Aroon Kongchoo

Specialty: Endocrinology

Endocrinology

አጠቃላይ ጤናችን ላይ ችግር የሚያመጣው የታይሮድ ችግር

 • Readers Rating
 • Rated 5 stars
  5 / 5 (1 )
 • Your Rating


No Comments

Sorry, the comment form is closed at this time.

Vejthani Hospital
Show PC ViewShow Mobile View