Customer Voice

Mrs Meselech

Share:

ወ/ሮ መሰለች ወጋሶ በህክምና ስሙ Locally Advanced Gastric Cancer በሚባል ህመም ስትሰቃይ የነበረ ሲሆን
ወደ ሆስፒታላችን ስትመጣ ምግብም ሆነ ፈሳሽ ነገር ማትወስድ የነበረ ሲሆን በቬጂታኒ ሆስፒታል ስፔሻሊሰቶች
በተደረገላት የተሳካ ህክምና ከህመምዋ እረፍት አግኝታ በሰላም ወደ ሀገር ቤት ተመልሳለች፡፡

‘’በሀገር ውስጥ ባደረግኩት ህክምና ጨጓራሽ ላይ ያለው ካንሰር በሰውነትሽ ተሰራጭቷል ተስፋ የለሽም ተብዬ የነበረ
ቢሆንም ወደ ታይላንድ ሀገር ቬጂታኒ ሆስፒታል መጥቼ በተደረገልኝ የህክምና እርዳታ ሁሉም ዶክተሮቼ ማለትም
ጠቅላላ ቀዶ ጠጋኝ ስፔሻሊስቱ ፤ የጨጓራ ስፔሻሊስቱ እና የካንሰር ስፔሻሊስቱ በጋራ ባደረጉልኝ ምርመራ እና የተሳካ
የህክምና ሂደት ከዛሬ ነገ ሬሳዋ ወደ ሀገር ቤት ይመጣል ተብሎ ሲጠበቅ ህይወቴ ተርፎ ሁለተኛ አልአዛር ሆኜ
በህይወት እና በጤና ወደ ሀገሬ ተመልሻለሁ፡፡ ወደ ውጪ ሀገር ለህክምና ስንመጣ የመጀመሪያችን ቢሆንም በቬጂታኒ
ሆስፒታል በቆየንበት ጊዜ ውስጥ ምንም አይነት የእንግድነት ስሜት ሳይሰማን ፍጹም ቤተሰባዊ የሆነ የህክምና
አገልግሎት አግኝተናል፡፡በመጨረሻም እኔና ቤተሰቤ ለመላው የሆስፒታሉ ባለሙያዎች መልካም የስራ ጊዜ በመመኘት
እና በታላቅ ምስጋና አስተያየታችንን እናጠቃልላለን፡፡’’

ወ/ሮ መሰለች ወጋሶ እና አቶ ታደለ ኩሳ

Mrs Meselech

  • Readers Rating
  • Rated 3.5 stars
    3.5 / 5 (3 )
  • Your Rating



Related Posts