3 መደበኛ የጡት ካንሰር ምርመራ ዘዴዎች
በጡት ካንሰር (Breast Cancer) የግንዛቤ ወር ውስጥ እራስዎን ያበረታቱ። ማሞግራም (Mammogram) እና ባዮፕሲዎችን ጨምሮ ስለ ውጤታማ የጡት ካንሰር ምርመራ
ከCOVID-19 በተጨማሪ የካንሰር በሽታ ሕክምናው መዘግየት እንደሌለበት ግንዛቤ ሊኖር ይገባል፡፡ ለጡት ካንሰር የሚሰጡ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምናዎችን እንይ፦
የጡት ካንሰር ሴቶችን ከሚያጠቁ በጣም የተለመዱ የካንሰር አይነቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የጡት ካንሰር እንደሌሎች የካንሰር ዓይነቶች በክብደት ደረጃው ሲለካ 4 ደረጃዎች አሉት፡፡ ከደረጃ 1-3 ያለ ካንሰር ማለት በመጀመሪያወች ደረጃ ያለ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ያልተሰራጨና መታከም የሚችል የካንሰር ደረጃ ነው፡፡ ደረጃ 4 የምንለው ደግሞ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የተሰራጨ ካንሰር ማለት ነው፡፡
1. ቀዶ ጥገና፦ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 ላሉ የጡት ካንሰር ዓይነቶች ቀዶ ጥገና ዋና ሕክምና ዘዴ ነው ፣ እንዲሁም ለተወሰኑ ደረጃ 4 ላይ ለደረሱ ኬዞችም ቀዶ ጥገና የህክምና ምርጫ ይሆናል። ሁለት ዓይነት የቀዶ ጥገና ዓይነቶች አሉ እነሱም፦ ካንሰር ያለበትን ቦታ ብቻ ለይቶ የማስወገድ ቀዶ ጥገና (Breast conservation surgery) እና በካንሰር የተጠቃውን ጡት ሙሉ በሙሉ የማስወገድ ቀዶ ጥገና (Mastectomy) ይባላሉ።
2. ሲስተሚክ ትሪትመንት (Systemic Treatment)፦ የካንሰር ሕዋሳት ለማከም በመላው ሰውነት ውስጥ የሚሰራጩ መድኃኒቶች ማለትም ኬሞቴራፒ፣ ሆርሞናል ቴራፒ እና ታርጌትድ ቴራፒ (HER2) በመጠቀም የሚደረግ ህክምና ነው፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት የሕክምና አማራጮች በተጨማሪ የጡት ካንሰርን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማከም የሚችሉ ሌሎች አዳዲስ መድኃኒቶችም አሉ፡፡
3. የጨረር ህክምና (Radiotherapy)፦ የጨረር ህክምና ከቀዶ ጥገናው በኋላ ካንሰሩ ተመልሶ
እንዳይመጣ እንዲሁም የተሻሉ ውጤቶችን ለማግኘት የካንሰር ሕዋሶችን ለመግደል ከፍተኛ መጠን ያለውጨረር በመጠቀም የሚከናወን ሕክምና ነው ፡፡ ለማጠቃለል ያህል የሚሰጠው ሕክምና በካንሰሩ ዓይነት ፣ ካንሰሩ በደረሰበት ደረጃ እንዲሁም በሽተኛው ያለበት አካላዊ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው ፡፡