የጤና መረጃዎች

የቬጅታኒ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ማዕከል አዲስ ምዕራፍ ጀምሯል

Share:

ለጀርባ አጥንት፣ musculoskeletal እንዲሁም የአጥንት ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የሚሰጠው ሁሉን አቀፍ ህክምና በአንድ ስፔሻሊስት ብቻ የሚሰጥ ሳይሆን የበርካታ ዲሲፕሊን የህክምና ቡድን ማለትም የአጥንት ህክምና ቡድን፣ ፊዚያትሪስቶችን፣ ፊዚዮቴራፒስቶችን እና occupational ቴራፒስቶችን ያካትታል።

ቬጅታኒ ሆስፒታል በቅርቡ የአጥንት ህክምና ማዕከል (Orthopedic Center)፣ የአከርካሪ ህክምና ማዕከል (Spine Center)፣ አጠቃላይ የመገጣጠሚያ ቅየራ ማዕከል (Total Joint Replacement Center)፣ ዘመናዊ የሪሃብሊቴሽን ማዕከል እንዲሁም የኢሜጂንግ ምርመራ ማእከልን ያካተተውን “የአጥንት ንጉስ – King of Bones” ህንፃ የከፈተ ሲሆን በሁሉም ክፍሎች አጠቃላይ ለአጥንት ችግሮች (Orthopedic problems) መፍትሄ መስጠት የሚያስችሉ ጠርዝ የሚቆርጡ ዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን አሟልተዋል። በተጨማሪም የሮቦቲክ ቴክኖሎጂን በተለያዩ ሁኔታዎች የምንጠቀም ሲሆን ከእነዚህም መካከል ለምርመራ፣ ለቀዶ ጥገና እንዲሁም ለሪሃብሊቴሽን አገልግሎት እንጠቀማለን።

የቬጅታኒ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ Charkrit Soucksakit, Ph.D እንደተናገሩት “የአጥንት ንጉስ – King of Bones” የተቋቋመው የአከርካሪ አጥንት፣ musculoskeletal እና የአጥንት ህመም (Orthopedic conditions) ላለባቸው ህመምተኞች አጠቃላይ መፍትሄን ለመስጠት አላማ ተደርጎ ነው። ከዘመናዊ ምርመራ ጀምሮ፣ ህክምና፣ ቀዶ ጥገና፣ እንዲሁም የሪሃብሊቴሽን አገልግሎቶች እጅግ ከፍተኛ ችሎታ እና ልምድ ባለው የሕክምና ቡድን በመታገዝ አገልግሎት እንዲሰጥ ታቅዶ የተገነባ ነው።

Charkrit Soucksakit፣ Ph.D በመጨመርም ቬጂታኒ ሆስፒታል በአጠቃላይ የጉልበት ቅየራ ፕሮግራም፣ በዳሌ ቅየራ ፕሮግራም፣ Lumbar Decompression and Fixation ፕሮግራም በታይላንድ የመጀመሪያው CCPC አክሪዴትድ የሆነ ሆስፒታል ሲሆን በቅርቡም በአጥንት ዘርፉ ድጋሜ እውቅና የተሰጠው (re-accreditation) ሆስፒታል ሲሆን የቬጅታኒ ሆስፒታል ‘የአጥንት ንጉስን’ የታካሚዎች የመጀመሪያ ምርጫ እንዲሆን አድርገነዋል ሲል ተናግሯል።

“የአጥንት ንጉስ” እንደ ኦ-አርም የቀዶ ጥገና ምስል ሲስተም (Intraoperative 2D/3D Imaging System) ፣ Surgical Navigator፣ በቀዶ ጥገና ወቅት የሚያገለግሉ Neuromonitoring እና ሌሎች ብዙ ጠርዝ በሚቆርጡ የህክምና ቴክኖሎጂዎች እና ሮቦቶች በመታገዝ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የአጥንት ህክምና ባለሙያዎች (Orthopedic surgeon) እጅ እጅግ የላቀ የአጥንት  ቀዶ (Orthopedic surgery) ጥገና ህክምናን ይሰጣል።

የአጥንት ቀዶ ጥገና ህክምናውን ከማዘመን ጎን ለጎን የቬጅታኒ ሆስፒታል ከቀዶ ጥገና በኋላ የሚሰጡ የሪሃብሊቴሽን ፕሮግራሞች በተከታታይ በማዘጋጀት እና በማሻሻል ላይ ይገኛል። እንዲሁም በሮቦት የታገዙ የእግር ጉዞ እና ሚዛን የመጠበቅ ስልጠና ማሽኖች እንደ Lokomat, C-Mill, እና Keeogo exoskeleton የመሳሰሉ የመንቀሳቀስ እና የመራመድ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ታቅደው የተዘጋጁ ማሽንኖችን በመጠቀም የሪሃብሊቴሽን ፕሮግራሞችን ይሰጣል።

Lokomat በነርቭ፣ በጡንቻ ወይም ከአጥንት ጋር በተያያዙ ችግሮች ምክንያት የሚከሰቱ እንደ ስትሮክ፣ የአከርካሪ ጉዳት/ቁስል፣ በአደጋ ምክንያት የተከሰተ የአንጎል ጉዳት እንዲሁም የፓርኪንሰን በሽታዎች ምክንያት  የመራመድ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች በአለም ላይ በቀዳሚነት የሚጠቀስ በሮቦት የሚታገዘ የእርምጃ ማሰልጠኛ ማሽን ነው። Lokomat ታካሚዎች ሰውነታቸው ያለውን ችሎታ እንዲያውቁት ለማድረግ የተለያዩ ሊያነቃቁ የሚችሉ ጨዋታ መሰል ልምምዶች በመጠቀም ተደጋጋሚ እና ውጤታማ የአካላዊ እንቅስቃሴ ስልጠናዎችን ይሰጣል። Lokomat ቴራፒ መሬት ላይ የመራመድ ችሎታን፣ የእርምጃ ፍጥነትን እና አቅምን፣ ሚዛንን የመጠበቅ፣ የእግሮቻችን ጡንቻ ጥንካሬን እንዲሁም የተሻለ ቀጣይ ህይወትን ያሻሽላል።

Keeogo exoskeleton ታካሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እርምጃ እንዲራመዱ እና ረዥም ርቀት እንዲጓዙ የሚያስችል ስማርት ፓወር  ኦርቶሲስ የእግር ጉዞ ድጋፍ ሰጪ መሣሪያ ነው። Keeogo እራስን ችሎ መራመድን እና ደረጃዎችን የመውጣት ችሎታን ያሻሽላል። የስትሮክ፣ የፓርኪንሰን በሽታ፣ ከፊል የአከርካሪ ጉዳት፣ የጉልበት osteoarthritis እንዲሁም በእርጅና ምክንያት የሚከሰተ የእንቅስቃሴ ችግር (geriatric) ያለባቸው Keeogo መጠቀም ይችላሉ።

C- Mill ተግባባራዊ የእርምጃ እና የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ ስልጠና ማሽን ባለ ዘመናዊ መገምገሚያ እና augmented and virtual reality ቴክኖሎጂ የስልጠና ትሬድሚል ማሽን ነው። C-Mill ታካሚዎች በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ውስት ለሚገጥሟቸው ተለዋዋጭ ሁኔታዎች እንዲሰለጥኑ እና ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል፣ ለምሳሌ በተጨናነቁ ቦታዎች ለመራመድ ወይም ሚዛናቸውን የመጠበቅ ችሎታቸውን ለማሻሻል የተለያዩ መሰናክሎችን የማስወገድ ስልጠና፣ የተስተካከለ እርምጃ እንዲኖር እንዲሁም ግንዛቤን ለመጨመር ያገለግላል።

በቬጅታኒ ሆስፒታል የፊዚያትሪስት ባለሙያ የሆኑት Assoc. Prof. Wasuwat Kitisomprayoonkul እንደተናገሩት የሪሃብሊቴሽን እና ፊዚካል ቴራፒ ሕክምና አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ወይም መንቀሳቀስ ለማይችሉ ታካሚዎች የሰውነታቸውን አቅም ለማሻሻል እና የህይወት ጥራትን ወደነበረበት ለመመለስ የሚደረግ ህክምና ነው። የሪሃብሊቴሽን ሜዲሲን እና ፊዚካል ቴራፒ ሕክምና በሽተኞች ያለማንም ድጋፍ ራሳቸውን መንከባከብ እና ብቻቸውን መንቀሳቀስ እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ይሁን እንጂ ባህላዊ የሪሃብሊቴሽን ዘዴ ሕክምናውን ውጤታማ እንዳይሆን የሚያደርጉ በርካታ ውስንነቶች አሉት በተለይም ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ላለባቸው ታካሚዎች ፊዚዮቴራፒስቱ በስልጠና ወቅት አካላዊ ድጋፍ ለማድረግ ከባድ ጥረቶችን ማድረግ ያስፈልገዋል። ታካሚዎቹም በእንደዚህ አይነት ሥልጠና ወቅት ድካም ይሰማቸዋል። ይህም ለረዥም ጊዜ ያለማቋረጥ ማሰልጠን እንዳይችሉ እና በቂ የሆኑ የእርምጃዎች እንዳይጓዙ ያደርጋቸዋል። ተጨማሪ እርምጃዎች/እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ neuroplasticity አለ ማለት ነው። እነዚህ ውስንነቶች ኖሩ ማለት ደግሞ ውጤታማነቱ ዝቅተኛ ይሆናል ማለት ነው።

በሮቦት የታገዘ የእርምጃ ስልጠና የተፈጠረው እነዚህን ውስንነቶች ለመፍታት ነው። በሮቦት መታገዝ ፊዚዮቴራፒስቱ በሽተኞችን ለታለመለት አላማ የሚሆኑ እና ተደጋጋሚ የተግባር ስልጠናዎችን እንዲያሠለጥን ይረዳዋል። ተደጋጋሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ስናደርግ ማዕከላዊ የእንቅስቃሴ ፓተርን አመንጭ የሆነውን ክፍል ያነቃቃል ይህም እንደ እርምጃ ያሉ ተደጋጋሚ የእንቅስቃሴ ፓተርን ያላቸውን ሂደቶች የሚቆጣጠረውን የነርቭ ስርዓት ያነቃቃል። ይህ አይነቱ አሰራር የታካሚውን እንቅስቃሴ ወደነበረበት ለመመለስ አጥጋቢ ውጤት ያመጣል። ተግባራዊ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን በማሻሻል፣ የእርምጃ ፍጥነት እና ጥንካሬን ከመጨመር አንፃር ከባህላዊ ሕክምና የተሻሉ ናቸው።

ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት ቬጅታኒ ሆስፒታል በአመት ውስጥ ከ100 ሀገራት ለሚመጡ ከ300,000 በላይ ታካሚዎችን አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። እንደ ቬጅታኒ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ Charkrit Soucksakit የአጥንት ንጉስ መመስረትን ምክንያት በማድረግ የታካሚዎችን ቁጥር በ100% ለመጨመር ያለመ ነው።

ምንጭ ባንኮክ ፖስት: https://www.bangkokpost.com/business/2171091/vejthani-hospital-commences-the-new-era-of-total-orthopedic-solutions

  • Readers Rating
  • Rated 3.6 stars
    3.6 / 5 (4 )
  • Your Rating
Related Posts