የጤና መረጃዎች

ሊምፎማ (Lymphoma) ከምናስበው በላይ እየበዛ የመጣ በሽታ ነው

Share:

ሊምፎማ (Lymphoma) በማንኛውም ሰአት ሊያጠቁን ከሚችሉ ከባድ በሽታዎች አንዱ ነው። ሊምፍኖዶች በሰውነታችን ውስጥ በሁሉም ቦታ ላይ ለምሳሌ፦ በአንገት፣ በብብታችን ውስጥ፣ ክርናችን ውስጥ፣ ጉልበት ውስጥ፣ ደረት ላይ እንዲሁም ሆዳችን ላይ ይገኛሉ። ከሁሉም በላይ የሊምፍ ሕዋሳት ወይም ሊምፎሳይትስ አንጀት ላይም ሆነ ሆድ ላይ በመላው ሰውነት ውስጥ ባሉ ሌሎች አካላቶቻችን ውስጥ ይኖራሉ። ስለዚህ ሊምፎማ በማንኛውም የሰውነታችን ክፍሎች ውስጥ ሊከሰት ይችላል።

ሊምፎማ (Lymphoma) መንስኤው እስካሁን አልታወቀም።

ይሁን እንጂ የሚከተሉት ለሊምፎማ አጋላጭ እንደሆኑ የታወቁ ምክንያቶች ናቸው (Lymphoma Risk factors)

  • እንደ ፀረ ተባይ እና የፀጉር ማቅለሚያ ኬሚካሎች
  • ዝቅተኛ ወይም የተዳከመ የበሽታ መከላከያ አቅም ያላቸው ለምሳሌ፣ የኤድስ በሽተኞች ፣ የአካል ንቅለ ተከላ ያደረጉ እና/ወይም የሪህ በሽተኞች
  • ዘረመል; ቤተሰብ ውስጥ በሊምፎማ ተይዞ የሚያውቅ ሰው ከነበረ

ትኩሳት ያለውና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ህመም የሌለው እብጠት፣ ድካም፣ ክብደት መቀነስ እና የሰውነት ደካማ መሆን የሊምፎማ ምልክቶች ምልክቶች ናቸው። ይሁን እንጂ እብጠት ሁል ጊዜ የካንሰር ምልክት ሊሆን አይችልም። ያልተለመዱ ነገሮችን ካስተዋሉ በአስቸኳይ የሕክምና ባለሙያ ማማከር አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም “ካንሰሩ ከመስፋፋቱ በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያለ ከታከመ ሊምፎማ ከፍተኛ የመዳን ዕድል አለው። ሕክምናው የኬሞቴራፒ ሕክምና ሲሆን ለአንዳንድ ሕመምተኞች ሐኪሙ የጨረር ሕክምናን እንደ ተጨማሪ ሊወስድ ይችላል።

  • Readers Rating
  • Rated 4.8 stars
    4.8 / 5 (2 )
  • Your Rating