የጤና መረጃዎች

የእግርዎ ጫማዎች ላይ ህመም ሲሰማዎ ህመሙን ለማስታገስ ሞቅ ባለ ወይም በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ እግርዎን ይዘፈዝፋሉ?

Share:

ቀኑን ሙሉ የእግር ጉዞ ሲያደርጉ ወይም ቆመው ሲውሉ የድካም ስሜት ሊሰማዎት እና በእግርዎ ጫማ ላይ ህመም ሊያስከትል ይችላል፡፡ ነገር ግን ህመሙን ለማስታገስ እግርዎን ለብ ባለ ወይም በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ዘፍዝፈውታል? እግርዎን በቀዝቃዛ ወይም በሞቀ ውሃ ውስጥ ለመዘፍዘፍ የተሻለው ጊዜስ መቼ ነው?

ቀኑን ሙሉ በእግር ሲጓዙ እና ለረዥም ጊዜ ቆመው በመዋልዎ ምክንያት በጫማዎ እና በእግሮችዎ ላይ ድካም እና ህመም ሲሰማዎት ጫማዎን እና እግሮችዎን “በቀዝቃዛ ውሃ” ውስጥ መዘፍዘፍ አለብዎ ምክንያቱም የደም ሥሮችዎን እንዲሰበሰቡ በማድረግና ብግነት የሚያስከትሉ ኬሚካሎችን ለመቀነስ ይረዳል። ይህን ተከትሎ በጡንቻዎች ላይ ያለው እብጠት እና መቆጣት ይቀንሳል።

እግርዎትን በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ለምን መዘፍዘፍ እንዳለብዎት አሁንም ግራ የሚገባዎት ከሆነ በገበያ ውስጥ የሚገኙትን የህመም ማስታገሻ ፕላስተሮች ወይም በጫማችን እና በእግራችን ላይ ጭነን ይምንይዛቸው ማቀዝቀዣዎችን (patches) እንዲመለከቱ እንመክርዎታለን። አብዛኛዎቹ ቀዝቃዛ እሽጎች ናቸው ምክንያቱም ጡንቻዎች ላይ የሚከሰት እብጠትን እና ብግነትን በማቀዝቀዝ መቀነስ ስለሚቻል ነው፡፡

እግራችን በሞቀ ውሃ ውስጥ ለመዘፍዘፍ ጥሩ የሚባለው ጊዜ መቼ ነው?

እግራችን ለብ ባለ ውሃ ውስጥ መዘፍዘፍ እግራችን ለማፍታታት ጥሩ ነው፡፡ ሞቅ ያለ ውሃ የደም ዝውውርን ሊያነቃቃ ስለሚችል በቀላሉ ለመተኛት ይረዳናል፡፡ ስለሆነም ዘና ለማለት እና የበለጠ ምቹ እንቅልፍ ለማግኘት ከፈለጉ ከ36 – 38 ዲግሪ ሴልሺየስ አካባቢ በሆነ ለብ ያለ ውሃ እግርዎን ከ10-15 ደቂቃ እንዲዘፈዝፉ እንመክርዎታለን። እዲሁም እግርዎን እስኪደርቅ ድረስ ይጥረጉት ከዚያ እግርዎን ቅባት (moisturizer) ይቀቡት ይህ የበለጠ ዘና እንዲሉ ይረዳዎታል።

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (3 )
  • Your Rating