የጤና መረጃዎች

የተራቀቁ የዕይታ ማስተካከያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጥርት ያለ እይታን ይጎናፀፉ

Share:

በዘመናችን ዕይታን ለማስተካከል የሚረዱ በርካታ አመቺ፣ ጊዜ የማይወስዱ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ  ቴክኖሎጂዎች አሉ፡፡ እነዚህ የዐይናችን ዕይታን ማስተካከያ ቴክኖሎጂዎች መነጽር ማድረግ ወይም ዓይን ላይ የሚለጠፉ ሌንሶችን ለማይፈልጉ ሰዎች ይመከራሉ፡፡

የዕይታ ማስተካከያ ሕክምና አማራጮች እንደሚከተለው ቀርበዋል;

  • Photorefractive Keratectomy (PRK): ረቲና ወደሚባለው የዓይን ክፍል የሚሄደውን የብርሃን አቅጣጫ ለማስተካከል የሚደረግ ቀዶ ጥገና ሲሆን ደረቅ ዐይን ወይም ቀጭን ኮርኒያ ላላቸው ሰዎች ተስማሚ የሆነ የዐይን ቀዶ ጥገና ነው፡፡ በቀዶ ጥገናው ወቅት የአይን የቀዶ ጥገና ሐኪሙ የኮርኒያውን የውጭ ሽፋን በልዩ መሳሪያ ወይም በኬሚካል ያላቅቃል፣ ከዚያ በኋላ ኮርኒያውን እንደ አስፈላጊነቱ ለማስተካከል excimer ሌዘር ይጠቀማል፡፡ ተለጣፊ ሌንሱን ዓይን ውስጥ በማስገባት ኮርኒያው እንዲሸፈን ያደርጋል፣ ነገር ግን ኮርኒያው በደንብ ሲያገግም ተለጣፊ ሌንሱ ይወገዳል።
  • Laser In-Situ Keratomileusis (LASIK): ይህ አይነቱ የሪፍራክቲቭ የአይን ቀዶ ጥገና ህክምና የቅርብ እይታ፣ የሩቅ እይታ እና የዓይን ብዥታ ችግር ለማስተካከል ያገለግላል። በLASIK ቀዶ ጥገና ወቅት የዓይን ቀዶ ጥገና ሃኪሙ የኮርኒያውን የውጨኛ ሽፋን ለማንሳት microkeratome የሚባል መሳሪያ ይጠቀማል በማስቀጠልም excimer ሌዘር በመጠቀም የኮርኒያውን መካከለኛ ክፍል ቅርፅ ያስተካክላል በመቀጠልም የኮርኒያው የውጨኛው ክፍል ወደነበረበት እንዲመለስ ይደረጋል።
  • Femtosecond – LASIK (FemtoLASIK): ይህ አይነቱ የሪፍራክቲቭ አይን ቀዶ ጥገና ህክምና ምንም አይነት ስለታማ ነገርን የማይጠቀም የ LASIK ህክምና ዘዴ ሲሆን በያንዳንዱ ደረጃ ሌዘር ይጠቀማል። የኮርኒያው የውጨኛው ክፍል በfemtosecond ሌዘር አማካኝነት ከተነሳ በኋላ መካከለኛው የኮርኒያው ክፍል በexcimer ሌዘር አማካኝነት የማስተካከል ስራ ይሰራለታል። FemtoLASIK ቀዶ ጥገና በጣም ውጤታማ እና አስተማማኝ ዋስትና ያለው በመሆኑ ታካሚዎች በፍጥነት እንዲያገግሙ ይረዳል።

የቅርብ እይታ ችግር፣ የሩቅ እይታ ችግር ወይም የዐይን ብዥታ ችግር ካለብዎት እንዲሁም መነፀር መልበስ ወይም ተለጣፊ ሌንስ መልበስ ከሰለቸዎት ወደ ቬጂታኒ ሆስፒታል የዓይን ክፍል በመምጣት እይታዎን ለማስተካከል የምክር አገልግሎት እንዲሁም ህክምና ያግኙ።ቀጠሮ ለማስያዝ በስልክ ቁጥር +66(0)2-734-0000 Ext. 2815, 3260 or +66(0)90-907-2560 (ለኢትዮጵያውያን የተዘጋጀ ስልክ ቁጥር) በመደወል ያነጋግሩን።

  • Readers Rating
  • Rated 3.2 stars
    3.2 / 5 (8 )
  • Your Rating