የጤና መረጃዎች

ምላጭ አልባ በሆነው Refractive(በአይን ውስጥ ያለ የብርሃን አቅጣጫ የማስተካከል) የዓይን ቀዶ ጥገና በመታገዝ ዓለምን ይበልጥ ጥርት ባለ እይታ ይመልከቷት – Femto LASIK

Share:

Femto LASIK ከየትኛውም አቅጣጫ ጥርት ያለ ዕይታ እንዲያገኙ የሚያስችልዎ ምላጭ አልባ የብርሃን አቅጣጫን የማስተካከል (Refractive eye surgery) የዓይን ቀዶ ጥገና ነው።

Femto LASIK ምንድን ነው?

በአሁኑ ጊዜ ከመነፀሮች እና ከተለጣፊ የእይታ ሌንሶች በተጨማሪ በጣም ብዙ እይታን ለማስተካከል የሚያገለግሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች አሉ። ለምሳሌ እንደ LASIK፣ Femto LASIK  እና Implantable Collamer Lens (ICL) ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ምላጭ አልባ refractive የዐይን የቀዶ ጥገና ዘዴ ወይም ደግሞ ፌምቶ ላሲክ (Femto LASIK ) በመባልም የሚታወቀው ለዓይን ይበልጥ ትክክለኛ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቾት ያለው በመሆኑ በጣም ተወዳጅ የአይን ቀዶ ጥገና ዘዴ ነው፡፡ በተጨማሪም Femto LASIK  ኮርኒያ የሚባለው የአይናቸው ክፍል ቀጭን የሆኑ፣ መጠኑ በደበኛ ያልሆነ ወይም እጥፋት ያለው ኮርኒያ እና ትናንሽ ዓይኖች ያላቸውን ሕመምተኞች ለማከም ያገለግላል፡፡

Femto LASIK , ምላጭአልባ የብርሃን አቅጣጫን የማስተካከል (Refractive eye surgery) የአይን ቀዶ ጥገና ከባህላዊው LASIK  ይለያል ምክንያቱም ባህላዊ LASIK ስንመለከት መቁረጫው ከስለታማ ነገር የተሰራና እይታን ለማስተካከል በሚደረገው የኮርኒያ ቅርፅ ማስተካከል ሂደት ላይ (Excimer laser) ኤክሳይመር ሌዘርን ይጠቀማል፡፡ በሌላ በኩል Femto LASIK  እያንዳንዱ ቀዶ ጥገና የሚከናወነው በሌዘር ጨረር ሲሆን የውጨኛውን ሽፋን ከማንሳት ጀምሮ የኮርኒያውን ቅርፅ እስከማስተካከል ድረስ ሌዘር ጨረርን ይጠቀማል፡፡ ስለዚህ Femto LASIK  ውጤታማና ከባህላዊው LASIK  የተሻለ ነው።

የFemto LASIK ጥቅሞች

LASIK የዕይታ ችግር ላለባቸው ሰዎች እንዲሁም የቅርብ እይታ ወይም የሩቅ እይታ ችግርን ለማስተካከል መነፅር እና ተለጣፊ ሌንሶችን በመልበስ የተጎዱ ሰዎችን መነፅር ወይም ተለጣፊ ሌንስ መልበስ ሳያስፈልግ የተሻለ ምቹ ህይወት እና ጥርት ያለ እይታ እንዲኖራቸው ለማስተካከል የሚያስችል ውጤታማ የሆነ አዲስ የፈጠራ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ምላጭ አልባ የብርሃን አቅጣጫን የማስተካከል (Refractive eye surgery) የዐይን ቀዶ ጥገና ወይም Femto LASIK ህክምና  አሰራሩ ለዓይን የበለጠ ምቹ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ፣ አጭር የቀዶ ጥገና ጊዜ የሚወስድ፣ ​​ከባህላዊው LASIK  የበለጠ አስተማማኝ፣ እንዲሁም ማደንዘዣ መርፌ መውጋት የማያስፈልገው ስለሆነ ምንም ዓይነት ጠባሳ እንዳያስቀርብን ሆኖ የተሰራ ነው። በተጨማሪም ኮርኒያ ላይ የመፋፋቅ (የኮርኒያ መበሳት) የመከሰት እድሉን ይቀንሳል፣ ኮርኒያ በፍጥነት እንዲድን እና አጭር የማገገሚያ ጊዜ ብቻ እንዲወስድ ያደርገዋል፡፡ ታካሚዎቹ እርግጠኛ መሆን ያለባቸው Femto LASIK በቋሚነት የዓይናቸውን የእይታ ችግር ወደ መደበኛው ወይም ከመደበኛው በተጠጋ መልኩ እይታቸው እንዲመለስ ማገዝ እንደሚችል ህክምና መሆኑን ነው፡፡

Femto LASIK  ህክምና ማድረግ የሚችሉት እነማን ናቸው?

Femto LASIK የእይታ ማስተካከያ ህክምና ለማድረግ ያሰቡ ሰዎች ቢያንስ ለ1 ዓመት የአይን እይታቸው በመልካም ሁኔታ የቆየ እና እንደ Keratoconus፣ ወይም ማኩላር ዲጄኔሬሽን ያሉ ከዓይኖች ወይም ኮርኒያ ጋር የተያያዙ በሽታዎች የሌለባቸው መሆን አለባቸው፡፡ ይሁን እንጂ ለእርስዎ የሚስማማዎትን ትክክለኛ ሕክምና ለማቀድ ሐኪምዎን እንዲያማክሩ ምክራችን ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በቬጂታኒ ሆስፒታል 2ኛ ፍሎር ላይ የሚገኘውን የዓይን ማዕከል ያነጋግሩ፤ በስልክ ቁጥር +66(0)2-734-0000 Ext. 2815 ወይም +66(0)90-907-2560 (ለኢትዮጵያውያን የተዘጋጀው ስልክ) ይደውሉ።

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (1 )
  • Your Rating