የጤና መረጃዎች

በአንጀት ውስጥ የሚገኝ ፖሊፕ (እባጭ) ካንሰር ሊሆን ይችላል (Colorectal cancer)

Share:

ዘመኑ የደረሰበት የህክምና እድገት ትልቁ አንጀት ላይ የሚፈጠሩ ፖሊፕስ የሚባሉ እባጮች ለአንጀት ካንሰር (Colorectal cancer) መንስኤዎች መሆናቸውን እንድናውቅ አስችሎናል። አብዛኛዎች ፖሊፕስ ያለባቸው በሽተኞች ፖሊፕሱ እስኪያድግና ወደ ካንሰር እስኪቀየር ምንም አይነት ምልክት የላቸውም። አሁን ላይ በአንጀት ውስጥ የሚገኝን ፖሊፕስ 2ሚሊ ሜትር መጠን ያለቸው ትንንሾች ቢሆኑ ወይም የባቄላ (mung bean) መጠን ያላቸው ቢሆኑ በኮሎኖስኮፒ መለየት ይቻላል። በተጨማሪም ጠባብ ባንድ ያላቸውን ምስሎች የሚያጎላልን (Magnifying Narrow Band Imaging) በአጭሩ Magnifying NBI ጋር በጋራ እንጠቀመዋለን።

ፖሊፕስ (አንጀት ላይ የሚወጣ እባጭ) መኖሩ በፊንጢጣ በኩል በሚገባ ካሜራ (Colonoscopy) ሲረጋገጥ ዶክተሩ ለወደፊት ፖሊፕሱ ወደ ካንሰር ከመቀየሩ በፊት ያስወግደዋል። ይሄን ማድረግ የትልቁ አንጀት ካንሰርን ለመከላከል በጣም ቀላል እና ውጤታማ ዘዴ ነው። ከኮሎኖስኮፒ በተጨማሪ ኢንዶስኮፒክ ሰብሙኮሳል ዲስሴክሽን (Endoscopic Submucosal Dissection) (ESD) የሚባል ፖሊፕ የምናስወግድበት የህክምና ሂደት አለ። ይህ የህክምና ሂደት በጣም ትልቅና ወደ ውስጥ ጠልቀው የገቡ ፖሊፕሶችን ለማስወገድ ያገለግላል። ምንም እንኳን የተወሰነው የፖሊፕስ ክፍል ወደካንሰር የተቀየረ ቢሆንም ወደ ንፍፊቶች (lymph node) ያልተሰራጨ ከሆነ ማስወገድ ይቻላል። ከኢንዶስኮፒክ ሰብሙኮሳል ዲስሴክሽን (Endoscopic Submucosal Dissection) ህክምና በሁዋላ ታካሚው ምንም አይነት ጠባሳ ሆዱ ላይ አይኖረውም፣ በተወሰኑት ላይ በሆድ በኩል የሚከፈት የሰገራ ማስወገጃ (colostomy) አያስፈልግም። ይሁን እንጂ ፖሊፕ የማስወገድ ህክምና ያደረጉ በሽተኞች ዶክተሩ በሚያዘው መሰረት በፊንጢጣ በኩል በሚገባ ካሜራ (colonoscopy) በሚደረግ ምርመራ ክትትል እንዲያደርጉ ይመከራል።

የኮሎኖስኮፒ ምርመራ ማድረግ የጤና ምርመራ ማድረግ ነው። ስለዚህ ችግሮች እስኪፈጠሩ መጠበቅ የለብንም በተለይ እድሜያቸው ከ50 አመት በላይ የሆኑ ወይም ቤተሰብ ውስጥ የአንጀት ካንሰር (Colorectal cancer) ተይዞ የነበረ ሰው ካለ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል። የኮሎኖስኮፒ ምርመራ (Colonoscopy) ከማድረግ በተጨማሪ ቀይ ስጋን ባለመመገብ፣ ለረዥም ጊዜ ቀዝቅዘው እና ፕሮሰስ የሆኑ ምግቦችን ባለመመገብ የአንጀት ካንሰር (Colorectal cancer) ተጋላጭነታችን መቀነስ እንችላለን። ለበለጠ መረጃ የአንጀትና ሬክተም ቀዶ ጥገና (Colorectal Surgery) ክሊኒክ  ያነጋግሩ; 3ኛ ፍሎር ቬጂታኒ ሆስፒታል; ወይም በስልክ ቁጥር +66(0)2-734-0000 ext. 4500, 4501. ይደውሉ።

  • Readers Rating
  • Rated 4.5 stars
    4.5 / 5 (1 )
  • Your Rating