Excellence in Healthcare and Inclusion
We are thrilled to announce that Vejthani Hospital has been recognized for its "Excellence in Healthcare and Inclusion" in Thailand
በታይላንድ ላይ ያለው የጉዞ እገዳ ከተነሳ በኋላ የህክምና እና የጤና ቱሪዝም ጉዞ የሚፈቀድ ይሆናል። ይሁን እንጂ በታይላንድ ህክምናቸውን ማድረግ የሚፈልጉ በሽተኞች በቅድሚያ ከቬጅታኒ ሆስፒታል ጋር በመገናኘትና የሚከተሉትን ዶክመንቶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አስፈላጊ የሆኑ ዶክመንቶችና መረጃወችን ከላኩልን በኋላ ቬጅታኒ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በ48 ሰዓት ውስጥ የምናመቻችልዎና ድጋፍ የምንሰጥዎ ይሆናል።
ቪዛ በሚያመለክቱበት ወቅት ታካሚው ከታች የተዘረዘሩትን አስፈላጊ ዶክመንቶች ማዘጋጀት ይኖርበታል:
ማስታወሻ፡ የቆንስላ ፅ/ቤት ኦፊሰሩ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነ ተጨማሪ ዶክመንቶችን የመጠየቅ መብት እንዳለው ማስታወስ አለብዎት ።
አንዴ ቪዛ እና የመግቢያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ከተሰጠዎት በኋላ ታካሚው የአማራጭ ሆስፒታል ኳራንታይን እናየቀጠሮ ወረቀት ለማግኘት ከበረራ ቀን በፊት 72 ሰዓት ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዶክመንቶች ለቬጅታኒሆስፒታል መላክ ይኖርበታል።
ታይላንድ እንደደረሱ ታካሚውም ሆነ አስታማሚው በሙቀት መለያው በኩል ማለፍ እንዲሁም ከታች የተዘረዘሩትን ዶክመንቶች ማቅረብ ይኖርብወታል፦
● የመግቢያ ሰርተፊኬት
● ሜዲካል ሰርተፊኬት / ሜዲካል ሪፖርት / መብረር እንደሚችሉ ማረጋገጫ የጤና ሰርተፊኬት (Fit to Fly) (ከበረራ በፊት ባሉት 72 ሰዓት ውስጥ የተሰጠ)
● ሜዲካል ሰርተፊኬት ከኮረና ምርመራ ውጤት ጋር (ኔጋቲቭ ነው/አያሳይም የሚል) (ከበረራ በፊት ባሉት 72 ሰዓት ውስጥ የተሰጠ)
● የጉዞ ሜዲካል ኢንሹራንስ (Medical Travel Insurance) (100,000 የአሜሪካን ዶላር/በ1ሰው)
● የፋይናንሺያል አቅም የሚያሳዩ ዶክመንቶች (ለምሳሌ የባንክ ስቴትመንት፣ የፋይናንሺያል ጋራንቲ ደብዳቤ ወዘተ.)
● የአማራጭ ሆስፒታል ኳራንቲን ማረጋገጫ ደብዳቤ
● T.8 ፎርም(http://www.thaiembassy.org/london/contents/filemanager/document/T8_form.pdf)
ታካሚው ከደንበኞች መዳረሻ በር ቁጥር 10 ላይ ከሚገኘው የቬጅታኒ ሆስፒታል ቢሮ በመምጣት እኛን ማግኘት ይችላል። ወደ ሆስፒታል ጉዞ ከማድረጋችን በፊት የሁሉም ሙቀት ይለካል ከ37.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ካልበለጠ ታካሚው በነፃ ትራንስፖርት ወደ ሆስፒታል ይላካል።
ቬጅታኒ ሆስፒታል እንደደረሱ ታካሚውም ሆነ አስታማሚው ከሆስፒታሉ የኮሮና ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ውጤቱ ኔጋቲቭ ወይም የማያሳይ ከሆነ ታካሚው ቢያንስ ለ14 ቀን ህክምናውን እየወሰደ ኳራንቲን ውስጥ ይቆያል አስታማሚውም በተመሳሳይ። በቬጅታኒ ሆስፒታል ቆይታዎ ልዩ ስልጠና በወሰደ የህክምና ቡድን ልዩ ድጋፍና የጤናዎትን ጉዳይም ሆነ ሌሎች ፍላጎትወትን በተመለከተ አስፈላጊወን እንክብካቤ ይደረግልወታል።
በቬጂታኒ ሆስፒታል የኳራንቲን ጊዜዎን ከጨረሱ በኋላ የሚከተሉትን ዶክመንቶች እንሰጥዎታለን:
በቀጥታ በዚህ https://www.facebook.com/VejthaniExpatsBangkok/ ወይም በኢሜይል አድራሻችን i[email protected] ወይም በቀጥታ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ማግኘት ይችላሉ: