የጤና መረጃዎች

ቺኩንጉንያ (Chikungunya)ማከምና መከላከል ይቻላል

Share:

ቺኩንጉንያ (Chikungunya) በአሁኑ ሰአት ታይላንድ ውስጥ በተለያዩ ቦታወች ላይ እየተከሰተ ያለና ምንም አይነት ፀረ-ቫይረስ ክትባትም ሆነ መድሃኒት ሊያድነው የማይችል በሽታ ነው። በሽታውን ልንከላከል የምንችልበት ዘዴ ራሳችን ከትንኝ ንክሻ በመከላከል ነው።

ዶክተር ቡድሳኮርን ዳራዋንኩል በቬጅታኒ ሆስፒታል የሪህማቶሎጂ ዶክተር እንደተናገሩት ቺኩንጉንያ (Chikungunya)  በቫይረስ የሚመጣ በሽታ ሲሆን ወደ ሰው የሚታላለፈውም በሽታውን በተሸከሙ ትንኞች አማካኝነት ነው። ቺኩንጉንያ (Chikungunya) ቫይረስ ያለበት በሽተኛ ከ3–7 ቀን የሚቆይ ትኩሳትና ሽፍታ እንዲሁም ከባድ የመገጣጠሚያ ህመም ይኖረዋል። በብዛት የእጅ እና የእግር መገጣጠሚያዎቹ ላይ ህመም፣ የጡንቻ ህመም፣ እንዲሁም የጀርባ ህመም ይስተዋላል። አንዳንድ ሰዎች ከባድ ህመም ሊያጋጥማቸው እንዲሁም ለመንቀሳቀስ፣ ለመቀመጥ ወይም መራመድ ሊቸገሩ፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግማ ሲቆይ ወደ መገጣጠሚያ ብግነት (osteoarthritis) ሊቀየር ይችላል።የበሽታው ክብደት ከተለያየ በሽተኛ ላይ የተለያየ ነው። አንዳንድ ሰወች ላይ ፅኑ የመገጣጠሚያ ህመም በማስከተል ለተከታታይ ሁለት አመት ያክል ህክምና ያስፈልጋቸዋል። አንዳንድ በሽተኞች ላይ ደግሞ ምንም ከባድ የሆነ ምልክት አያሳይም ፓራሲታሞል ወይም ሌላ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት በመውሰድ ህመሙ በሁለት ሳምንት ውስጥ ይሻሻላል ወይም ሊድን ይችላል። በተለያዩ የእድሜ ደረጃዎች ውስጥ የሚኖረው የህመም ምልክት የተለያየ ነው። ለምሳሌ እድሜያቸው ከሁለት አመት በታች የሆኑ በቺኩንጉንያ (Chikungunya) ቫይረስ የተያዙ ህፃናት ህመሙ ሊፀናባቸው ይችላል። በአንፃሩ ደግሞ እድሜያቸው ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ልጆች እንዲሁም ወጣቶች ላይ ትኩሳት፣ ሽፍታ፣ እንዲሁም ከባድ ያልሆኑ የመገጣጠሚያ ህመም ብቻ ሊያስከትል እንዲሁም እድሜያቸው ከገፉና ከውልደት ጀምሮ የጤና ችግር ኖሮባቸው አሁን በበሽታው ከተያዙ ሰወች ጋር ሲነፃፀር ከሽታው በፍጥነት ይድናሉ።

ዶክተር ቡድሳኮርን እንደገለፁት በአሁኑ ሰአት ቺኩንጉንያ (Chikungunya) ምንም አይነት ፀረ-ቫይረስ ክትባትም ሆነ መድሃኒት በሽታውን ሊከላከለው ወይም ቫይረሱን ሊገድለው አይችልም። ህክምናው የሚያተኩረው ህመሞችን እንዳይኖሩ መቆጣጠር ነው።

ቺኩንጉንያ (Chikungunya) ወደ ሰው የሚታላለፈው በሽታውን በተሸከሙ ትንኞች አማካኝነት ነው። ትንኟ በበሽታው ከተያዘ ከ4-5 ቀን የሆነን ሰው ማለትም በመጀመሪያው ትኩሳት የሚያሳይበት ወቅት ከነደፈች በኋላ ሌሎችን ሰዎች ከነደፈች የተነደፉት ሰዎች በበሽታው ይያዛሉ። አሁን ላይ በሽታው ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ምንም አይነት ሪፖርት የለም። ይሁን እንጂ አንዴ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ሰውነታቸው በሽታውን ለመከላከል ኢሚውኒቲ ይኖረዋል ነገር ግን በቀጣይ በበሽታው ላለመያዛቸው ማረጋገጫ የለም።በሽታውን ለመከላከል የተሻለው መንገድ ራስን ከትንኝ ንክሻ መከላከል እንዲሁም በመኖሪያ አካባቢያችን ያሉ የትንኝ መራቢያ ቦታወችን በማጥፋት ትንኝ እንዳይራባ በማስቆም መሆኑን ዶክተር ቡድሳኮርን ይመክራሉ።

  • Readers Rating
  • Rated 4.8 stars
    4.8 / 5 (3 )
  • Your Rating

Related Posts