የጤና መረጃዎች

በአነስተኛ ቀዶ ጥገና የሚከናወን የመጀመሪያ ደረጃ የትልቁ አንጀት ካንሰር ህክምና

Share:

አብዛኛው የትልቁ አንጀት ካንሰር ወይም የሬክተም እና የትልቁ አንጀት ካንሰር የሚጀምረው በትልቁ አንጀት ግድግዳ ላይ በሚፈጠር ኮሎሬክታል አዲኖማ በሚባል እባጭ አይነት ነገር ነው፡፡ በቬጂታኒ ሆስፒታል ጠቅላላ እና የትልቁ አንጀት እና ሬክተም ቀዶ ጠጋኝ እንደሆኑት እንደ ዶክተር አውቻይ ካንጃናፕቲክ ይህ የትልቁ አንጀት ካንሰር በጊዜ ካልታከመ ወደ ጡንቻ እና ከጡንቻ ስር ያሉ የሰውነት አካላት ድረስ ዘልቆ ሊያድግ ይችላል ይላሉ፡፡

እንደ ዶክተሩ ገለጻም ምልክቶቹ ከሰገራ ጋር የሚወጣ ደም፤ የሆድ ህመም፤ የሰገራ መቅጠን እንዲሁም የሚቀያየር የመጸዳዳት ልማድ የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡የበሽታው ምልክቶችም እንደ እባጩ በሰውነት ውስጥ የሚገኝበት ቦታ እንዲሁም ወደ ሌላ የሰውነት አካላት የመሰራጨት ስፋት ይለያያሉ፡፡ከፊንጢጣ የሚወጣ ደም ወይም ምንጩ ያልታወቀ የደም ማነስ ህመም ለትልቁ አንጀት እና ሬክተም ካንሰር ተጋላጭ መሆናችንን ጠቋሚ ምልክቶች ሲሆኑ በቤተሰብ አባላት ላይ የካንሰር ህመም ተከስቶ የሚያውቅ ከሆነ፤ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ታካሚዎች እንዲሁም ሲጋራን የሚያጨሱ ሰዎች ለዚህ በሽታ በይበልጥ ተጋላጭ ሲሆኑ ይታያል፡፡

የትልቁ አንጀት እንዲሁም የሬክተም ካንሰር ህመምን ለመለየት የምንጠቀምባቸው የተለያዩ መንገዶች ሲኖሩ እንደ የሰገራ ምርመራ ፤የኢንዶስኮፒ ምርመራ፤እንዲሁም በጣም በስፋት የምንጠቀመው ኮሎኖስኮፒ(Colonoscopy)የተባለውየመመርመሪያ መንገድ ይጠቀሳሉ፡፡የአንጀት እና የሬክተም ካንሰር ላለባቸው ሰዎች ቀዶ ጥገና የመጀመሪያው ህክምና ሲሆን እንደ ካንሰሩ ደረጃ እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ደግሞ ታካሚው በተጨማሪ የመድሃኒት ህክምና(Chemotherapy) እና የጨረር ህክምና(Radiation therapy) ሊደረግለት ይችላል፡፡

በቀደሙት ጊዜያት ይህን አይነት በሽታ ያለበት ሰው ትልቅ የቀዶ ጥገና ማድረግ ያስፈልገው የነበረ ሲሆን በዚህም ምክኒያት ለአላስፈላጊ የሆድ ላይ ጠባሳ እንዲሁም በሰውነት ክፍል በኩል በሚደረግ ክፍተት ይከናወን ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ይህ ህክምና የሚከናወነው ላፓራስኮፒ እና ኢንዶስኮፒ በተባሉት ዘመናዊ መሳሪያዎች በመታገዝ ስለሆነ ቀዶ ጥገና እንደ ቀድሞ ጊዜ አስፈሪ አይሆንም ፡፡

ይህ የትልቁ አንጀት እና ሬክተም ካንሰር በጊዜ ከተደረሰበት ምንም ጠባሳ ሳይተው በሚከናወነው የኢንዶስኮፒክ ህክምና በመታገዝ ሊታከም ይችላል፡፡የተወሰነ የትልቁ አንጀት ክፍላቸው ላይ ቀዶ ጥገና ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ደግሞ በአነስተኛ ቅድ በሚከናወን ቀዶ ጥገና ህመሙን መቀነስ እና ታካሚው በአጭር ጊዜ ማገገም እንዲችል ማድረግ ይችላል፡፡

ታሞ ከመማቀቅ እንደሚባለው ዶ/ር አውቻይ አክለውም ይህ የትልቁ አንጀት እና ሬክተም ካንሰርን መደበኛ አጠቃላይ የጤና ምርመራ በማድረግ፤ጤነኛ የአኗኗር ዘይቤን በመከተል እንዲሁም አመጋገብን በማስተካከል መከላከል ይቻላል ሲሉ ሀሳባቸውን ደምድመዋል፡፡

በአነስተኛ ቀዶ ጥገና የሚከናወን የመጀመሪያ ደረጃ የትልቁ አንጀት ካንሰር ህክምና

ስለ ሌሎች የካንሰር አይነቶች ለምሳሌ ስለ የሳምባ ካንሰር መረጃ ለማግኘት ይሄን ይጫኑ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

  • Readers Rating
  • Rated 4.6 stars
    4.6 / 5 (4 )
  • Your Rating