የጤና መረጃዎች

የካንሰር አቫታር (አምሳያ) – ፕረሲዥን (ትክክለኛ) የካንሰር ሕክምና

Share:

በአጠቃላይ ካንሰርን በመድሃኒት ለማከም የታካሚው ሰውነት ለተሰጡት መድሃኒቶች እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ ለማየት የጥበቃ ጊዜን ይፈልጋል። ምላሹ እንደተጠበቀው ካልሆነ የመድሃኒት አይነት መቀየር ሊያስፈልግ ይችላል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ የካንሰር አቫታር (አምሳያ) የተባለ አዲስ ህክምና ከህክምናው ሂደት ጀምሮ ትክክለኛ እና ተስማሚ መድሃኒቶችን ለታካሚዎች ለማቅረብ ያገለግላል።

በቬጅታኒ ሆስፒታል ሜዲካል ኦንኮሎጂስት የሆኑት ዶ/ር ቪግሮም ጄኔቲሲን እንደገለፁት ካንሰር በፕረሲዥን ሜዲስን (ሕክምና) ወይም ግላዊነትን በተላበሰ የሕክምና ዘዴ ሲታከም የዘር ምርመራዎች በካንሰር ሕዋሳት ውስጥ የተከሰቱትን ሚውቴሽን (ለውጦች) ለማግኘት እንደሚደረጉ አብራርተዋል። የምርመራው ውጤትም ለሐኪሙ በጣም ተስማሚ የሆኑትን መድሃኒቶች ለመወሰን እንደ መረጃ ሆኖ ያገለግላል። ምንም እንኳን ፕሪሲሽን ሜዲስን (ሕክምና) ለየግል የተበጀ ሕክምና ቢሆንም መድኃኒቶች ከተሰጡ በኋላ ታካሚው ለእነዚያ መድኃኒቶች የሚሰጠው ምላሽ ለተወሰነ ጊዜ ክትትል ሊደረግበት ይገባል። ታካሚው በሰውነቱ ውስጥ የካንሰር ሕዋሳትን ለይቶ የሚያውቅ የሲቲ ስካን ምርመራ ይደረግለታል። ለህክምናው የሚሰጠው ምላሽ ደካማ ከሆነ ወይም የሚጠበቀውን የማያሟላ ከሆነ የሕክምናውን ውጤታማነት ለመጨመር ጥቅም ላይ የዋሉ መድሃኒቶች አይነት መቀየር ሊያስፈልግ ይችላል።

ተመራማሪዎች በአሁኑ ጊዜ የተለየ ዘዴ አግኝተዋል። የካንሰር አቫታር (አምሳያ) ለታካሚው ከመሰጠቱ በፊት

የእያንዳንዱን መድሃኒት ምላሽ ለመፈተሽ ይተገበራል። የካንሰር አቫታር (አምሳያ) ከታካሚው ላይ የካንሰር ሕብረህዋሳትን በመሰብሰብ እና በላብራቶሪ ውስጥ በማልማት በሰውነቱ ውስጥ ካሉ የካንሰር ሕዋሳት ጋር እስኪመሳሰሉ ድረስ እንዲያድጉ የማድረግ የሕክምና ዘዴ ነው። በቤተ ሙከራ ውስጥ ያለው የካንሰር ሕዋስ በታካሚው አካል ውስጥ ያሉትን የካንሰር ሕዋሳት ይወክላል። እነዚያ የተወከሉት የካንሰር ሕዋሳት በታካሚው ላይ በግል የተለየ ሕክምና ከመደረጉ በፊት ለእያንዳንዱ ዓይነት የካንሰር ሕክምና እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ ለማየት ይመረመራሉ።

የካንሰር አቫታር (አምሳያ) ካንሰር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለሆነባቸው ፣ ህመማቸው ቀድሞውኑ ለተሰራጨ እና በመደበኛ ህክምና ዘዴዎች ለምሳሌ እንደ ቀዶ ጥገና ፣ ጨረር ወይም በካንሰር መድሃኒቶች በጠቅላላው ጥሩ ምላሽ ላላገኙ ታካሚዎች ጠቃሚ ነው። በዚህ ጊዜ ታካሚዎች ከመደበኛው የተለየ አዲስ የሕክምና ዘዴ ወይም አዲስ የካንሰር መድሐኒቶች ሊፈልጉ ይችላሉ።

የካንሰር አቫታር (አምሳያ) ትክክለኛዎቹን መድሃኒቶች ለመወሰን ጥቅም ላይ ይውላል ፣ ይህም የታካሚዎችን በራስ መተማመን እና የሕክምናውን ትክክለኛነት ይጨምራል። ለምሳሌ 10 የኬሞቴራፒ ዓይነቶች ከታካሚው የካንሰር በሽታ አምጪ ተህዋስያን ጋር የሚጣጣሙ ከሆነ ዶክተሩ የእያንዳንዱን የኬሞቴራፒ ዓይነቶች በካንሰር አቫታር (አምሳያ) ያለውን ውጤታማነት እና ምላሽ ይመረምራል። ይህም ታካሚው እነዚህን ሁሉ 10 ዓይነቶች መሞከር ሳያስፈልገው ሐኪሙ ለካንሰሩ በጣም ተስማሚ የሆነውን የኬሞቴራፒ ዓይነት እንዲወስን ወይም እንዲመርጥ ያስችለዋል።

በካንሰር አቫታር (አምሳያ) የተመረመረ መድሃኒት ጥሩ ምላሽ ከሰጠ ይህ መድሃኒት በታካሚው ላይም አዎንታዊ ተጽእኖ የመፍጠር እድሉ ከ70-80% ነው።

“በታካሚው ላይ ያለው የመድኃኒት ምላሽ መጠን በተወከሉት ሕዋሳት ላይ ካለው ምላሽ መጠን ጋር 100% የማይመሳሰልበት ምክንያት የመድኃኒቱን ምላሽ የሚወስኑ የተለያዩ ምክንያቶች ስላሉ ሲሆን በተለይ ደግሞ የሰውነት ውስጣዊ ሁኔታ ዋነኛው ነው። ለምሳሌ አንዳንድ መድኃኒቶች ወደ ሰውነታችን በሚገቡበት ጊዜ በደም ስር ውስጥ ወይም በሌላ መንገድ ይሰራጫሉ ፣ ይህም በምርመራው ላይ እንደታየው ጉልህ ውጤት ያስገኛል።” ዶክተር ቪግሮም

ለጥያቄዎች ወይም ቀጠሮ ለመያዝ በአማርኛ የስልክ መስመር ይደውሉልን፡ +66 (0) 90-907-2560

  • Readers Rating
  • Rated 4.5 stars
    4.5 / 5 (1 )
  • Your Rating