የጤና መረጃዎች

የሬዙም የውሃ ትነት ሕክምና – ምንም ቀዶ ጥገና ሳያስፈልግ ለቤኒን ፕሮስታቲክ ሃይፐርፕላዝያ ወይም ፕሮስቴት እጢ የሚደረግ ዘመናዊ ሕክምና

Share:

ቤኒን ፕሮስታቲክ ሃይፐርፕላዝያ ወይም የፕሮስቴት እጢ የሽንት ችግር ምልክቶችን ለምሳሌ እንደ ዳይሱሪያ ፣ ብዙ ጊዜ በሌሊት ሽንት ፣ እንዲሁም ፊኛን ባዶ አለማድረግ ወይም ሽንትን መያዝ አለመቻልን ያስከትላል። እነዚህም የታካሚዎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት ሊያስተጓጕሉ ይችላሉ።

በአሁኑ ጊዜ ሬዙም የውሃ ትነት ህክምና ተብሎ የሚጠራው የውሃ ትነት ቴክኖሎጂ ቤኒን ፕሮስታቲክ ሃይፕላዝያን ወይም የፕሮስቴት እጢን ለማከም ያገለግላል። በፕሮስቴት አመንጪ ዕጢ ዙሪያ ከመጠን በላይ ያሉ ሕብረ ሕዋሳትን ለማጥፋት የሙቅ ውሃ እንፋሎትን የሚጠቀም ቀዶ ጥገና ያልሆነ ሕክምና ነው።

የሬዙም የውሃ ትነት ሕክምና ጥቅሞች

  1. ምንም ቀዶ ጥገና አያስፈልግም ስለዚህ ምንም አይነት ቀዳዳ አይኖርም
  2. ማደንዘዣ አያስፈልግም
  3. ከ10-15 ደቂቃዎች ብቻ ይወስዳል
  4. በሆስፒታል ውስጥ ምንም የሌሊት ቆይታ የለም
  5. የሕክምናው ውጤት እስከ 5 ዓመት ድረስ ይቆያል
  6. የህይወት ዘመን መድሃኒቶችን አስፈላጊነት ያስወግዳል
  7. በመደበኛ ቀዶ ጥገና ምክንያት በጾታዊ ተግባራት ላይ የሚከሰቱ ችግሮች ጉልህ መሻሻል ይኖራቸዋል

የሬዙም የውሃ ትነት ሕክምና በሽንት ቱቦ ውስጥ ትንሽ መርፌን ወደ ፕሮስቴት አመንጪ ዕጢ በማስገባት ይከናወናል። ከዚያም ዶክተሩ እንፋሎቱን በ 106 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ወደ እጢው ውስጥ ከ6-10 ጊዜ በእያንዳንዱ ጊዜ ለ9 ሰከንዶች ይለቃል። ትኩሱ ትነት ሽንት ቱቦን የሚዘጉ የፕሮስቴት አመንጪ ዕጢ ሴሎችን ለማጥፋት ይበተናል። ከዚያ በኋላ የሰውነት ተፈጥሯዊ ፈውስ ሂደት የሞቱ ሴሎችን ይቀበላል። ይህ አሰራር ከ4-6 ሳምንታት ውስጥ ምልክቶችን ያሻሽላል።

ለበለጠ መረጃ እባክዎን የኡሮሎጂ ማእከልን ያነጋግሩ ፣
ቬጅታኒ ሆስፒታል. ይደውሉ 02-734-0000 የውስጥ መስመር. 4500
የአማርኛ ስልክ መስመር: +66 (0) 90-907-2560

  • Readers Rating
  • Rated 3.3 stars
    3.3 / 5 (2 )
  • Your Rating




Related Posts