የጤና መረጃዎች

ውጤታማ ህክምናዎችን በማድረግ ለስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) ችግርዎ መፍትሄ ያግኙ

Share:

ስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) ጎልማሳ ወንዶች ላይ የሚከሰት የተለመደ የወሲብ ችግር ሲሆን አንድ ሰው የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ለመፈፀም በሚያስችለ መልኩ ብልቱን አጠንክሮ ማቆም አለመቻል ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚገምቱት ታይላንድ ውስጥ ከ50% በላይ የሚሆኑ ጎልማሳ ወንዶች በተወሰነ ደረጃ የስንፈተ ወሲብ  (Erectile Dysfunction) ችግር አለባቸው፣ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ደግሞ ለችግሩ ከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው፡፡

ስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) ያጋጠማቸው ወንዶች በብልታቸው ርዝመት ሙሉ በሚገኘው corpora cavernosa በተባለው ስፖንጅ ህብረ ህዋስ የማያቋርጥ የደም ፍሰት ላይኖር ይችላል።

የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) ምክንያቶች አእምሯዊ ወይም አካላዊ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ቀጣይ የሆነ የደም ፍሰት እንዲኖር ለማድረግ የሚያግዙ በርካታ ውጤታማ ህክምናዎች አሉ፡፡

ለስንፈተ ወሲብ አጋላጭ ምክንያቶችሳይኮጂካዊ ምክንያቶች

ጤናማ አካላዊ ጤንነት ያላቸው ወንዶች ለስንፈተ ወሲብ የመጋለጥ ዕድላቸው አነስተኛ ነው፡፡ እንደ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ እና ድብርት ያሉ የአእምሮ ሕመሞች ለስንፈተ ወሲብ ችግር ዋና አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ ከግንኙነት ጉዳዮች ጋር ተያይዘው የሚመነጩ ቀለል ያሉ ወይም ጊዜያዊ የአእምሮ ጤና ችግሮች እንዲሁ አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

በቂ እንቅልፍ አለማግኘት

በእንቅልፍ ወቅት ሰውነትዎ ማረፍ እና እራሱን ማደስ ይችላል፣ አንጎልዎን እና ጡንቻዎችዎን ከረጅም እና ከባድ ድካም ዕረፍት ይሰጣቸዋል፡፡ በቂ እንቅልፍ ሰውነትዎ ራሱን እንዲስተካክል እና ደምዎ በመደበኛ ደረጃ እንዲፈስ ይረዳል።

እንደ sleep apnea እና insomnia ያሉ የእንቅልፍ ችግሮች ሰውነትዎ በእንቅልፍ ወቅት ራሱን ለማደስ የሚያደርገውን ተግባር ያስተጓጉላሉ። በቂ እንቅልፍ የማያገኙ ወንዶች የአእምሮ ድካም እና የጡንቻዎች አለማረፍ ችግር ያጋጥማቸዋል፣ ይሄን ተከትሎ በወሲባዊ እንቅስቃሴ ወቅት ስንፈተ ወሲብን ያስከትላል፡፡

አካላዊ እንቅስቃሴ ያልበዛበት ወይም የሌለው የአኗኗር ዘይቤ

በዋነኝነት እንቅስቃሴ የማይጠይቅ የአኗኗር ዘይቤን የሚመሩ ወንዶች ለስንፈተ ወሲብ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ቀን ላይ አብዛኛውን ጊዜ መቀመጥ ወይም መተኛት ጡንቻዎትን በአግባቡ እንዲንቀሳቀሱ አያደርግም ወይም የልብ ምትዎን ፍጥነት ከፍ አያደርግም። እነዚህ ሁለቱ ሰውነታችን ጠንካራ የልብና የደም ስር ሲስተም እንዲኖረው የምናደርግባቸው መንገዶች ናቸው፡፡

የልብና የደም ቧንቧ ችግር ያለባቸው ወንዶች የደም ፍሰታቸው ደካማ ሊሆን ይችላል ይህን ተከትሎ ወሲብ ለማድረግ የሚያስፈልገው ጥንካሬ አይኖራቸውም፡፡

የሆርሞን ችግሮች

ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች ብልት እንዲቆም ዋነኛ መነቃቃት ይፈጥራሉ፡፡ ቴስቶስትሮን የወንዱን የወሲብ ፍላጎት እንዲነሳሳ የሚያደርግ እና ዝቅተኛ ቴስቶስትሮን ሲከሰት ደግሞ የወሲብ መነቃቃት እንዳይፈጠር አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል፡፡

የቴስቶስትሮን መጠን በእርጅና፣ በቫይታሚኖች እና ማዕድናትን እጥረት፣ ሲጋራ በማጨስ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ባለመስራት እንዲሁም በሌሎች ብዙ ምክንያቶች ሊዛባ ይችላል፡፡

የልብና የደም ስር (ካርዲዮቫስኩላር) ችግሮች

የካርዲዮቫስኩላር እና የስርዓተ ልመት ችግሮች የልብ በሽታ፣ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ኮሌስትሮል እና የደም ዝውውር መዘጋትን ጨምሮ ለስንፈተ ወሲብ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፡፡

የስንፈተ ወሲብ ሕክምና አማራጮች (Treatment Options for Erectile Dysfunction)

ለስንፈተ ወሲብ ችግር የተለያዩ ውጤታማ የሕክምና ዘዴዎች አሉ፡፡ በጣም የተለመደው የመድሃኒት ህክምና ሲሆን መድኃኒቶችም Tadalafil እና Sildenafil ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት መድሃኒቶች ጡንቻዎችን እና የደም ቧንቧዎችን ለማፍታታት የሚያገለግሉ በከፍተኛ ሁኔታ የተዘጉ የደምስሮችን የሚከፍቱ መድሃኒቶች ናቸው፡፡ የብልት መቆምን እንዲረዳ ወደ ብልት የሚሄደውን የደም ዝውውርን ይጨምራሉ፡፡ ከወሲብ ማነቃቂያ ጋር በአንድ ላይ ሰውየው ብልቱን ማቆም እንዲችልና እንዲቆይ ይረዱታል፡፡

ሌሎች የስንፈተ ወሲብ ሕክምናዎች extracorporeal shock ሕክምና እና platelet-rich plasma (PRP) ሕክምና ናቸው፡፡ ሁለቱም አማራጭ ህክምናዎች ለአዳዲስ የደም ሥሮች እድገት መነቃቃት እና ነባር የተደፈኑ የደምስሮች ላይ የዘጋውን ነገር ለመሰባበር በወንዱ ብልት ላይ የሚተገበሩ የህክምና አማራጮች ናቸው፡፡

በዝቅተኛ ቴስትሮስትሮን መጠን ለሚቸገሩ ወንዶች አብዛኛውን ጊዜ ቴስትስትሮን በተፈጥሮ ሂደቱ እንዲመረት የሚያደርጉ (testosterone precursors) ወይም በተፈጥሯዊ መንገድ ቴስትሮስትሮን እንዲመረት በሚያግዙ ሌሎች ቫይታሚኖች እና ተዋጽኦዎች ይታከማሉ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ሐኪሙ ቴስቶስትሮን የመተካት ሕክምና እንዲደረግ ሊመክር ይችላል፡፡

በቬጅታኒ ሆስፒታል ሃኪም ለማማከር ቀጠሮ ይያዙ

በማንኛውም ደረጃ ላይ ያለ የስንፈተ ወሲብ ችግር ካጋጠመዎ በቬጂታኒ ሆስፒታል የቬጂታኒ Q-life ማዕከልን ያነጋግሩ እንዲሁም ሃኪም ለማነጋገር ቀጠሮ ይያዙ፡፡ ሐኪሞቻችን የችግራችሁን ዋና መንስኤ በመፈለግ እና ለእርስዎ በጣም ውጤታማ የሆነውን የህክምና አማራጭን ለማግኘት ይሰራሉ​​፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 2.3 stars
    2.3 / 5 (6 )
  • Your Rating



Related Posts