የጤና መረጃዎች

ኮምፒውተር ላይ የሚሰሩ ሰዎችን ከሚያጠቁ በጣም ከተለመዱ ዋነኛ ችግሮች መካከል ካርፓል ተነል ሲንድረም (Carpal Tunnel Syndrome (CTS)) አንዱ ነው

Share:

ከእጃችን ጣቶች መልክት ተቀብሎ ወደጭንቅላት በሚወስደው ነርቭ ላይ የሚከሰት ጫና (Median nerve compression) ወይም እጃችን አንጓ ላይ በሚገኙ ካርፓል በሚባሉ አጥንቶችና ጅማቶች መካከል በሚገኝ መተላለፊያ ላይ የሚከሰት ህመም (Carpal Tunnel Syndrome (CTS)) የሚከሰተው ካርፓል ተነል የተባለው መተላለፊያ ላይ እብጠት ሲከሰት፣ በመዳፋችን በኩል ያለው የእጃችን አንጓ አካባቢ ያለው መተላለፊያ እየጠበበ ሲመጣ፣ ተደጋጋሚ በሆነ የእጅ እንቅስቃሴ ወይም እጃችን ወደ አንድ አቅጣጫ አጥፈን ለረዥም ጊዜ በመቆየት ምክንያት የሚከሰት ነው፡፡ ካርፓል ተነል ላይ መቆጣት (inflammation) ሲከሰት በእጃችን መካከል በሚያልፈው ሚዲያን ነርቭ ላይ ጫና ይፈጥራል። ሚዲያን ነርቭ ለአውራጣታችን፣ ጠቋሚ ጣት፣ መካከለኛው ጣት እና ለግማሽ የቀለበት ጣታችን ክፍል ነገሮችን የመንካት ስሜት እንዲኖር ያግዛል፡፡ ወደ አውራ ጣት ለሚሄዱ ጡንቻዎች መልዕክት የሚደርሳቸው እንዲሁ በመካከለኛ ነርቭ (median nerve) አማካኝነት ነው፡፡

ካርፓል ተነል ላይ በሚከሰት ከፍተኛ ግፊት ሚዲያን ነርቭ ላይ ጫና ሲያድርበት እጃችንና የእጣታችን ጎን ላይ የመደንዘዝ፣ የመድከም፣ የህመም እና የማቃጠል ስሜት እንዲሰማን ያደርገናል። እንዲሁም እኩለ ሌሊት ላይ ወይም ጠዋት ከእንቅልፍ በነቃን ሰዓት ወይም እጃችን ያለማቋረጥ ከተጠቀምን በኋላ እጃችን ላይ የኤሌክትሪክ ንዝረት አይነት ህመም ሊሰማን ይችላል፡፡ ምልክቶቹ ከባድ በሚሆኑበት ጊዜ የማያቋርጥ ህመም ሊያጋጥም ይችላል፡፡ የካርፓል ተነል ሲንድሮም (Carpal Tunnel Syndrome (CTS)) በጡንቻዎች ምላሽ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል እንዲሁም በምንጨብጥበት ጊዜ ጥንካሬ መቀነስ እና ዕቃዎችን ለመሸከም የመቸገር ወይም ብዙ ጊዜ እቃዎች ከእጃችን የማምለጥ ሁኔታዎች ይከሰታሉ፡፡ በዋናነት በካርፓል ተነል ውስጥ የሚገኘው አያያዥ ህብረህዋስ (fascia) ተግባር የእጅዎን አንጓ ጥንካሬን ከፍ ለማድረግና የእጅን ክብደት/ ኃይል ለመቆጣጠር እንዲሁም በመተላለፊያው ውስጥ ያሉት ጅማቶች ተግባር ውጤታማ እንዲሆን መርዳት ነው። ይሁን እንጂ በእጅዎን ለረጅም ጊዜ የሆነን ነገርን ከመጠን በላይ አጥብቀን መያዝ የካርፓል ተነል መቆጣትን ይስከትላል፡፡ መተላለፊያ ተነሉ median nerve ሊጫን ወደሚችልበት አቅጣጫ ከ3-4 ሚሊ ሜትር ድረስ ሊያብጥ ይችላል፡፡ የካርፓል ተነል ሲንድሮም (Carpal Tunnel Syndrome (CTS)) በተለምዶ እጆቻቸውን ረዘም ላለ ጊዜ ወደ አንድ አቅጣጫ አጥፈው በሚጠቀሙ እና በተደጋጋሚ ንዝረት ያላቸው መሣሪያዎችን በሚያንቀሳቅሱ ሰዎች ላይ ይከሰታል ሲሉ የphysical medicine እና የሪሃብሊቴሽን ዶክተር የሆኑት Dr. Nararit Luanchumrorn ይናገራሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለመያዝ ዘመናዊ የሪሃብሊቴሽን ማዕከላችን ያነጋግሩ፣ አድራሻችን ቬጂታኒ ሆስፒታል የአጥንት ንጉስ ህንፃ ከ5ኛ – 6ኛ ፎቅ ያገኙናል ወይም በስልክ ቁጥር +66(0)90-907-2560 ይደውሉ (የአማርኛ መስመር)፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (2 )
  • Your Rating