የጤና መረጃዎች

የኮረና (COVID-19) ክትባት ከመወሰዱ በፊት በሚወሰድበት ወቅት እና ከመወሰዱ በኋላ ማወቅ ያለብዎት ነገር

Share:

ክትባት ከመወሰዱ በፊት

  • ስለ COVID-19 ክትባቶች መረጃዎችን ያንብቡ ከዚያም ለክትባት ቀጠሮ ይያዙ፡፡
  • በቂ እንቅልፍ ይውሰዱ፣ ቢያንስ 8 ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፣ እንዲሁም አልኮል እና ካፊን የያዙ መጠጦችን ያስወግዱ፡፡
  • እርጉዝ ሴቶች ወይም ነፍሰ ጡር ስለመሆናቸው ጥርጣሬ ያላቸው ሴቶች የCOVID-19 ክትባት መከተብ የለባቸውም፡፡
  • ሥር የሰደደ በሽታ ያለባቸው ታካሚዎች ሐኪሙ እንዲያቆሙ እስካላዘዘ ድረስ ከCOVID-19 ክትባት በፊት መድኃኒት መውሰዳቸውን ማቆም የለባቸውም፡፡
  • ከCOVID-19 ክትባት በፊት የሰውነትዎን ሙቀት ይለኩ፡፡ ከፍተኛ ትኩሳት ካለብዎ ቀጠሮውን ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፉ እንመክራለን፡፡

ክትባት በሚወሰድበት ወቅት

  • ለCOVID-19 ክትባት ዝግጁ ይሁኑ፣ ከመሄድዎ በፊት ምግብ ይመገቡ፡፡
  • ከላይ የምንለብሳቸው አልባሳት ክንዳችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችሉ ይሁኑ፡፡
  • የሚጋሯቸውን ነገሮች ለመቀነስ የራስዎን እስክርቢቶ ያዘጋጁ፡፡
  • ወደ COVID-19 ክትባት ቦታ ከክትባት ሰዓት ቢያንስ 15 ደቂቃዎች ቀድመው ይገኙ፡፡
  • የሕክምና ታሪክዎን ለህክምና ባለሙያዎች በዝርዝር ይንገሩ (ለምሳሌ የጤና ሁኔታዎ፣ የመድሃኒት አለርጂ፣ የክትባት አለርጂ፣ የምግብ አለርጂ፣ የደም መፍሰስ ችግሮች እና ማንኛውም የሚያሳስቡዎት በሽታዎች ካሉ ያሳውቁ)
  • የአፍ ጭምብል ይልበሱ፣ ርቀትዎን ይጠብቁ፣ እንዲሁም ክትባቱን ከመውሰድዎ በፊት፣ በክትባት ወቅት እና ከክትባት በኋላ እጅዎን ይታጠቡ፡፡

ክትባት ከተወሰደ በኋላ

  • ክትባት ከተከተቡ በኋላ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ የተከሰተ አዲስ የስሜት ለውጥ ካለ ያስተውሉ፡፡
  • የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊከሰቱ ስለሚችሉ የCOVID-19 ክትባት ከሌሎች የክትባት ዓይነቶች ጋር በአንድ ጊዜ መከተብ የለብዎትም፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ዓይነት ክትባት ሲወጋ በክትባቶች መካከል ቢያንስ የ1ወር ልዩነት መኖር አለበት፡፡
  • ትኩሳት ወይም የጡንቻ ህመም ካጋጠመዎ፣ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ወይም ፓራሲታሞል 500mg በየ6 ሰዓት ልዩነት ህመሙን ለማስታገስ መውሰድ ይኖርብዎታል (Brufen፣ Arcoxia፣ Celebrex የተሰኙትን መድሃኒቶች እንዳይወስዱ) እንዲሁም ብዙ ውሃ መጠጣት እና እረፍት ማድረግ አለብዎት፡፡
  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (1 )
  • Your Rating




Related Posts