የጤና መረጃዎች

የታይሮይድ በሽታ (Thyroid Disease) ለሕይወት አስጊ የሆነ በሽታ ነው

Share:

ያልተለመደ የምግብ መፈጨት (metabolism) ችግር ፣ የስሜት መለዋወጥ እና የፀጉር መነቃቀል ያጋጥሙዎታል? እነዚህ የታይሮይድ በሽታ (Thyroid disease) ምልክቶች ናቸው። ለወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል አሁንኑ ምርመራ ማድረግና የሕክምናን አገልግሎት ማግኘት አለብዎት፡፡

ታይሮይድ (Thyroid gland) በሰው አካል ውስጥ ትልቁ የኢንዶክራይን እጢ ነው የሚገኘውም በአንገታችን በፊት ለፊት በኩል ከማንቁርታችን (Adam’s apple) ስር ነው፡፡ ታይሮይድ የቢራቢሮ ቅርፅ ያለው እጢ ሲሆን ለምግብ መፈጨት፣ ለነርቭ፣ ለሰውነት ሙቀት፣ እና ባህሪያችን መቆጣጠር የሚያስችለውን የታይሮይድ ሆርሞን ያመነጫል። ከተጠቀሱት በተጨማሪ ከልብ ተግባር፣ አጥንት፣ እና ጡንቻወች ተግባር ጋር የተገናኘ ነው።

በቬጂታኒ ሆስፒታል የኢንዶክሪኖሎጂ እና ሜታቦሊዝም ሀኪም የሆኑት ዶክተር አሩን ኮንግቾ እንደተናገሩት የታይሮይድ በሽታ (Thyroid disease) በሁለት ይከፈላል እነሱም የታይሮይድ ሆርሞን በብዛት መመረት (Hyperthyroidism) ወይም በሌላ አጠራሩ ታይሮቶክሲኮሲስ (Thyrotoxicosis) ወይም ታይሮይድ ከሚገባው በላይ ምላሽ መስጠት (Overactive Thyroid) በመባል የሚታወቀው ሲሆን ሌላኛው ችግር ደግሞ የታይሮይድ ሆርሞን በዝቅተኛ ሁኔታ መመረት (Hypothyroidism) በሌላ አጠራሩ ታይሮይድ ከሚገባው በታች ምላሽ መስጠት (Underactive Thyroid) በመባል ይታወቃል። ሀይፐርታይሮይዲዝም (Hyperthyroidism) ከፍተኛ የሆነ የታይሮይድ ሆርሞን በማምረት ከባድ ችግሮችን ያስከትላል ለምሳሌ ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ላብ፣ የባህሪ መቀያየር፣ ክብደት መቀነስ፣ የልብ ድካም፣ እንዲሁም በጣም ሲከፋ እስከ ሞት ያደርሳል። የሀይፖታይሮይዲዝም (Hypothyroidism) ችግር በሚኖርበት ጊዜ ደግሞ የሚመረተው የታይሮይድ ሆርሞን ለሰውነታችን ከሚያስፈልገው በታች የሚያደርግና ወደ ሃሽሞቶ ታይሮይዳይተስ (Hashimoto’s Thyroiditis) (በአውቶኢሚውን ችግር ምክንያት ታይሮይድ እጢ ላይ የሚፈጠር ብግነት) የሚያመራ የሚከተሉትን ችግሮች የሚያስከትል በሽታ ነው እነሱም በቀላሉ የድካም ስሜት መሰማት፣ እንቅልፍ እንቅልፍ የማለት፣ በቀላሉ የክብደት መጨመር እና የፀጉር መነቃቀል ችግሮችን ያስከትላል።

የታይሮይድ በሽታ (Thyroid disease) እስካሁን መንስኤው ምን እንደሆነ ግልፅ አይደለም ነገር ግን ከዘር ጋር የተያያዘና በብዛት ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ የሚከሰት በሽታ ነው። የታይሮይድ በሽታ በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ ሊፈጠር ይችላል ነገር ግን እድሜያቸው ከ 30-60 ዓመት በሆኑት ላይ በብዛት ይከሰታል።  ለትክክለኛ ምርመራ ሃኪሙ የታካሚውን ያለፈ ታሪክ ከመጠየቅ መጀመር አለበት ከዛም  በአካል ሰውየውን መመርመር (body examination)  እና የታይሮይድ ሆርሞን መጠንን ለማወቅ የደም ምርመራ መደረግ አለበት። ከምርመራ በኋላ ዶክተሩ የሚዋጡ መድሃኒቶችን እንዲወሰዱ ያዛል፣ ነገር ግን ሀይፐርታይሮይዲዝም ችግር ላለባቸው በሽተኞች የታይሮይድ እጢ ችግርን ወደነበረበት መጠኑን ለመቀነስ የተለመዱ መድሃኒቶች በትክክል አልሰራ ካሉ ወይም መድሃኒቱ ለበሽተኛው አለርጂ ከሆነበት የራዲዮአክቲቭ አዮዲን  እንደ ተጨማሪ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል። ከሀይፐርታይሮይዲዚም እና ከሀይፖታይሮይዲዝም በተጨማሪ ሌላኛው ከታይሮይድ እጢ ጋር የተያያዘው በሽታ የታይሮይድ እጢ መጠን መጨመር ወይም በሌላ አጠራር የእንቅርት በሽታ ነው። ምንም እንኳን የእንቅርት በሽታ በብዛት ህመም የሌለው ቢሆንም በምንውጥበትና በምንተነፍስበት ወቅት ያስቸግራል። የታይሮይድ ግላንድ ላይ እጢ ከወጣ የወጣው እጢ ከ 4-5% ካንሰር የመሆን እድል ይኖረዋል። በመሆኑም ሃኪሙ ሶስት አማራጮች ያሉትን የቀዶ ጥገና ህክምና ሊያደርግ ይችላል እነሱም; ሰውነት ተቀዶ የሚደረግ ቀዶ ጥገና፣ ብዙም ሰውነታችን ሳይቀደድ ለመሳሪያ ማስገቢያ ብቻ የሚሆን ተቀዶ የሚደረግ ቀዶ ጥገና (minimally invasive surgery) ፣ እና በአፍ በኩል በሚገባ ኢንዶስኮፒ የሚደረግ ቀዶ ጥገና () ናቸው። ካንሰራማ ካልሆነ ግን ቀዶ ጥገና ማድረግ አስፈላጊ አይደለም። ነገር ግን እንደ እጢው መጠን፣ እንዳለው ምልክት እና እንደ ዶክተሩ ውሳኔ የሚከናወን ይሆናል ሲሉ ዶክተር አሩን ይናገራሉ።

ራስዎን በመመልከት ከእነዚህ ምልክቶች እንዳሉብዎት ያረጋግጡ:

 • በቀላሉ መድከም
 • የልብ ምት መፍጠን ስሜት
 • የባህሪ መቀያየር
 • የእንቅልፍ መዛባት
 • የተጋነነ የሰውነት ላብ
 • የፀጉር መርገፍ
 • የጥፍር መነቀል
 • ቶሎ ቶሎ የርሃብ ስሜት መሰማት ወይም የምግብ ፍላጎት ማጣት
 • ያተለመደው ልክ ያልሆነ ሰገራ
 • ማቅለሽለሽና ማስመለስ
 • ለአጭር ጊዜያት የሚቆይ የክብደት መቀነስ ወይም ክብደት መጨመር
 • የወር አበባ ዑደት መዛባት

ይሁን እንጂ አብዛኛዎች በሽተኞች የሚታይ ምልክት ላይኖራቸው ይችላል; ነገር ግን የደም ምርመራ በማድረግ ወይም አመታዊ የጤና ምርመራ በማድረግ ማወቅ ይቻላል። የታይሮይድ በሽታ አለብኝ  ብለው ከተጠራጠሩ ወዲያውኑ ምርመራ ማድረግና አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ ይኖርብዎታል።

 • Readers Rating
 • Rated 2.3 stars
  2.3 / 5 (18 )
 • Your Rating