የጤና መረጃዎች

የተለመደው (ባህላዊ) የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና (Traditional Hemorrhoidectomy) እና የፊንጢጣ ኪንታሮት ሌዘር ህክምና (Laser Hemorrhoidectomy)

Share:

የፊንጢጣ ኪንታሮት (Hemorrhoid) የዕለት ተዕለት ኑሯችንን ላይ ተፅእኖ የሚያሳድርና በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ሊኖረንን የሚገባውን ደስታ ሁሉ የሚያሳጣና የሚረብሽ በሽታ ነው። በተለይም ከ3ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ላይ የደረሰ የፊንጢጣ ኪንታሮት በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ችግሩ የከፋ ይሆናል፡፡ ከ3ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ላይ የደረሰ የፊንጢጣ ኪንታሮት በሽታ ካለብዎት የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ህክምና (hemorrhoidectomy) ማድረግ ያስፈልግዎታል፡፡ ነገር ግን የትኛው ዓይነት የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚስማማዎት አስበው ያውቃሉ?

የተለመደው (ባህላዊ) የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ህክምና (Traditional Hemorrhoidectomy)

  • የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ከመካሄዱ በፊት በሕክምናው ወቅት የሚኖረውን ሕመም ለመቀነስ እና ህክምናው በሚከናወንበት ወቅት ታካሚው እንዳያውቅ ዶክተሩ ሙሉ ማደንዘዣ ወይም ወደ አከርካሪ አጥንት መቅኒ (ኤፒዱራል) ውስጥ የሚወጋ ማደንዘዣ መርፌ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና የሚያደርግ በሽተኛ በቀዶ ጥገናው ወቅት ህመም አይሰማውም ነገር ግን ከቀዶ ጥገናው በኋላ ህመምተኛው ከ5 -7 ቀናት ያህል በሆስፒታል ውስጥ መቆየት ያስፈልገዋል፡፡ ስለሆነም ባህላዊውን (የተለመደው) የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ህክምና መውሰድ ከፈለጉ የሕክምና ዕቅድዎን ቀድመው ማዘጋጀት ያስፈልግዎታል። ከዚህም በተጨማሪ ባህላዊውን የፊንጢጣ ኪንታሮት ሕክምና ያደረገ በሽተኛ በፊንጢጣው ላይ በቀዶ ጥገናው ምክንያት የሚከሰት ጠባሳ ይኖረዋል፡፡

የፊንጢጣ ኪንታሮት ሌዘር ቀዶ ጥገና ህክምና (Laser Hemorrhoidectomy)

  • Laser hemorrhoidectomy የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ህክምና አዲስ የፈጠራ ዘዴ ነው ፡፡ እንደ ባህላዊው የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ህክምና ሁሉ የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ከመካሄዱ በፊት በሕክምናው ወቅት የሚኖረውን ሕመም ለመቀነስ እና ህክምናው በሚከናወንበት ወቅት በሽተኛው እንዳያውቅ ዶክተሩ ሙሉ ማደንዘዣ ወይም ወደ አከርካሪ አጥንት መቅኒ (ኤፒዱራል) ውስጥ የሚወጋ ማደንዘዣ መርፌ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ በዚህ ዓይነቱ የፊንጢጣ ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ህክምና ወቅት ጫፍ ላይ የሉትን የፊንጢጣ ኪንታሮቱ ደም ወሳጅ ቧንቧዎችን ቅርንጫፎች ለማስወገድ ሌዘሩ በፊንጢጣ ቦይ ወደ ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል፡፡ ሌዘር ሄሞሮይዴክቶሚ ውበትን ከመጨመር አንፃር ውጤታማ ነው ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምክንያት የሚከሰት ምንም ዓይነት ጠባሳ ፊንጢጣ ላይ አይኖርም፡፡ የጨረር ሄሞሮይተክቶሚ ህክምና ከባህላዊ የፊንጢጣ  ኪንታሮት ቀዶ ጥገና ጋር ሲነ ፃፀር በሽተኛው አነስተኛ ህመም እና በቶሎ የማገገም (1-2 ቀናት) እድል አለው።

ለበለጠ መረጃ እባክዎት ቬጂታኒ ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘውን የጠቅላላ ቀዶ ጥገና ክፍልን ያነጋግሩ ስልክ +66(0)2-734-0000 ext. 4500, 4501

  • Readers Rating
  • Rated 3.5 stars
    3.5 / 5 (6 )
  • Your Rating




Related Posts