የጤና መረጃዎች

የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) መታከም ይችላል!

Share:

በእጃችን ጉረሮአችን (ታይሮይድ የሚገኝበት) አካባቢ ስንነካው እባጭ ካገኘን ይህ እባጭ ካንሰራማ የሆነ የታይሮይድ እባጭ ሊሆን ይችላል። ሳይታከሙ ከተውት በአካባቢው ወዳሉ የሊንፍ ኖዶች እና አጥንቶች ሊሰራጭ ይችላል። ነገር ግን አይጨነቁ መታከም ይችላል!

የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) ባልተለመደ የታይሮይድ ሴሎች መቀየር ምክንያት የሚከሰት በሽታ ነው። በመጀመርያው ደረጃ ላይ ያለ የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) በሚኖርበት ጊዜ በሽተኛው በብዛት በታይሮይድ እጢ አካባቢ እባጭ ይኖረዋል። በጊዜ ሂደት መጠኑ እየጨመረ እየጨመረ ወይም እየበዛ ይሄዳል። ሳንታከም ከተውነው ወደተለያየ የሰውነት ክፍል ይሰራጫል።

በቬጅታኒ ሆስፒታል የካንሰር ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር Thanate Dejsakdipon እንደሚያብራሩት ታይሮይድ ካንሰር ምልክቶችን የማሳየት እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው። ይሁን እንጂ በጣም የተለመዱት የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) ምልክቶች የሚከተሉ ናቸው ታይሮይድ እጢ ላይ እባጭ መፈጠር፣ ለመዋጥ መቸገር፣ የድምፅ መቀየር፣ እንዲሁም ድካም ወይም አንዳንድ ሰዎች ላይ የክብደት መቀነስ ናቸው። ታይሮይድ እጢ ላይ እባጭ ከተገኘ ለማረጋገጥ የአልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ያልተለመደና ጤናማ ያልሆነ ነገር መኖር አለመኖሩ ይረጋገጣል። የካንሰር ስፔሻሊስቱ የታይሮይድ ህዋሱን ለመመርመርና የካንሰር ሴል መኖሩን ለማረጋገጥ ኒድል ባዮፕሲ (needle biopsy) ይጠቀማል።

በዋናነት የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) ቀስ እያለ የሚያድግ በሽታ ነው። ነገር ግን ወደሌሎች የሰውነት ክፍሎች ከተሰራጨ በብዛት የሚሰራጨው ወደ ሊምፍኖዶች እና አጥንት ነው። ለታይሮይድ ካንሰር ተጋላጭ ከሚያደርጉ ነገሮች በዋናነት በከፍተኛ ደረጃ የጨረር ተጋላጭነት፣ የእድሜ መጨመር፣ እንዲሁም ከቤተሰብ አባል ውስጥ የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer)የተያዘ ሰው ከነበረ ናቸው። ዶክተር Thanate Dejsakdipon እንዳሉት የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) በብዛት የሚከሰተው እድሜያቸው ከ40 – 60 በላይ ባሉ ሰዎች ላይ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ የሚሰጠው የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) ህክምና የታይሮይድ ቀዶጥገና ህክምና ነው። ከቀዶጥገና በኋላ ዶክተሩ እባጩ ምን እንደሆነ ያረጋግጣል። ካንሰር መሆኑን ካረጋገጠ የካንሰር ሴሉን ለመግደልና ለወደፊት ተመልሶ የመምጣት እድሉን ለመቀነስ ዶክተሩ የራዲዮአክቲቭ አዮዲን ህክምና (radioactive iodine treatment) ሊያደርግለት ይችላል። የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) መታከም ይችላል ከ 70 – 80% በላይ የሚሆኑት የታይሮይድ ካንሰር (Thyroid cancer) በሽተኞች ምንም እንኳን ካንሰሩ ወደሌላ የሰውነት ክፍል ቢሰራጭም ህክምናቸው ግን ስኬታማ ነው። ከህክምና በኋላ በሽተኛው ከካንሰር ዶክተሩ ጋር በየጊዜው ክትትል ማድረግና የካንሰር ተጋላጭነት መኖሩን ለማረጋገጥ የካንሰር የደም ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። የታይሮይድ ካንሰርን (Thyroid cancer) ለኬሚካሎች እና ለጨረር ያለንን ተጋላጭነት በማስወገድ እንዲሁም አዮዲንን በአስፈላጊው መጠን በመጠቀም መከላከል ይቻላል። የታይሮይድ እጢ ወይም ጉሮሮወት አካባቢ ያልተለመደ ነገር ወይም እባጭ ካለ ምርመራ እንዲያደርጉና እንዲታከሙ በፅኑ ይመከራል።

  • Readers Rating
  • Rated 3.4 stars
    3.4 / 5 (5 )
  • Your Rating


Tags:


Related Posts