የጤና መረጃዎች

ኦቫሪያን ሲስት

Share:

ይህ ሁኔታ በአብዛኛው በሴቶች ላይ የሚፈጠር የእንቁላል ልቀት ሂደትን ከሚያስተጓጉሉ ተጠቃሽ ምክኒያቶች አንዱ ነው፡፡ይህም ማለት አንድሮጅን የተባለው ሆርሞን ከመጠን በላይ እንዲመረት በማድረግ የወር አበባ ኡደት መዛባትን ማለትም አንዳንዴ የሚፈስ የወር አበባ ወይም ደግሞ ፈጽሞ የወር አበባ መቅረትን በማስከተል ይገለጻል፡፡የእንቁላል አለመለቀቅ ችግር  የሴት መሃንነትን በማምጣት ከሚጠቀሱ ምክኒያቶች ቀዳሚውን ደረጃ ይይዛል፡፡

የኦቫሪያን ሲስት ህመም የወር አበባ በሚያዩ ሴቶችም ሆነ ባረጡ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በአብዛኛው ግን በመውለድ እድሜ ክልል ላይ ያሉ ሴቶች ላይ በስፋት ይስተዋላል፡፡

የህመሙ ምልክቶች

በታችኛው የሆድ አካባቢ ድንገተኛ የማይታገስ ህመም፤ክብደት መጨመር፤ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ፤ የዳሌ አጥንት ህመም፤የማህጸን ህመም፤የታችኛው ጀርባ ላይ የሚሰማ ህመም የተለመዱ ምልክቶች ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የሆድ መንፋት፤የጡት ህመም፤የወር አበባ በሚመጣበት ሰዓት እንዲሁም ካለቀ በኋላ የሚሰማ ህመም፤የወር አበባ መዛባት፤ከማህጸን የሚፈስ ያልተለመደ ደም ፤ በፊት ላይ እንዲሁም በሰውነት ላይ የጸጉር መብቀል እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

የህክምና አማራጮች

በኣቫሪ ላይ የሚወጣ ፈሳሽ ህክምና እንደ ሲስቱ መጠን እና ታማሚዋ እንደሚኖርዋት የህመም ስሜቶች የሚለያይ ሲሆን በበሽታው ምክኒያት የሚከሰት ህመምን በህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች ጊዜያዊ መፍትሄ ምግኘት የሚቻል ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በቤት ውስጥ ሊደረጉ የሚችሉ ለምሳሌ ሞቅ ያለ ሻወር መውሰድሙቅ ውሃ ውስጥ የተነከረ ጨርቅ ወይም በሙቅ ውሃ የተሞላ ጠርሙስ በታችኛው የሆድ ክፍል ማድረግ የተወጣጠሩ ጡንቻዎችን ዘና በማድረግ እና የደም ዝውውርን በማስተካከል ህመሙን ለማስታገስ ይረዳሉ፡፡

ከሁለት ወይም ሶስት የወር አበባ ኡደት በላይ የሚቆይ ፈሳሽ መቋጠር ወይም ደግሞ ያረጡ ሴቶች ላይ የሚከሰት ህመም የተወሳሰበ ችግር አመልካች ሊሆን ስለሚችል በአልትራሳውንድ እንዲሁም በላፓራስኮፕ በሚገባ ሊመረመር ይገባል፡፡በተለይም ደግሞ ከቤተሰብ አባላት መካከል ተመሳሳይ ህመም ተከስቶ የሚያውቅ ከሆነ እንደዚህ አይነት ህመም በቀዶ ጥገና የሚደረግ የናሙና ምርመራ ሊያስፈልገው ይችላል፡፡በዚህ የቀዶ ጥገና ሂደትም አንዳንዴ የተቋጠረውን ፈሳሽ ብቻ ለይቶ ማስወገድ ሲቻል እንደአስፈላጊነቱ ደግሞ የእንቁላል ማምረቻ ኦቫሪም አንዱ ወይም ሁለቱም ተቆርጦ አብሮ ሊወጣ ይችላል፡፡